ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የተባለው የኮቪድ ነገር ውሸት ነው ብዬ ነው የማስበው፤ ሁላችንም ላይ ትንሽ የአዕምሮ ተፅኖ ፈጥሮብናል”➖ሐብታሙ ገዛኸኝ

የሲዳማ ቡና ዛሬ ተጋጣሚውን አዳማ ከተማን 3ለ 0 አሸንፎ ወጥቷል። ከተቆጠሩት ሶስት ጎሎች ሁለተኛዋን ሀብታሙ ገዛኸኝ ነበር ያስቆጠረው ። በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ የሀብታሙ ወንድም ባዬ ገዛኸኝ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤን ሁለት ለባዶ ሲያሸነፍ አንዷን  ጎል ያስቆጠረ ተጨዋች ነበር። በተመሳሳይ ሀብታሙ ገዛኸኝ በምሽቱ ጨዋታ ጎል ቀንቶታል። ተጨዋቹ ከሱፐር ስፓርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጎ ነበር።
ወንድሜህ ጎል አስቆጥሮ ነበር? የትኛው ያምራል?
 በፈገግታ አዎ ጎሉን አይቼዋለሁ። የኔ ጎል ያምራል ብዬ አስባለሁ። (በፈገግታ) አላዳላሁም ….
ከባዬ ጎልና ካንተ ቤተሰብ በየትኛው ይደሰታል?
” መጀመሪያ ያየሁት የሱን ጎል ነው። እንደ ታላቅም ወደ እሱ ጎል የሚያደሉ ይመሥለኛል ቤተሰቦቼ። ወደ እሱ ያደላሉ ብዪ አስባለሁ።
እንደቤተሰብ ተፎካክራችሁ ተውቃላችሁ በጎል አስቆጣሪነት ?
“አምና ተፎካክረን ነበረ። እሱ ሲያገባ እኔም አገባለሁ። እስኪቋረጥ ድረስ ሁለታችንም ዘጠኝ ጎል አግብተን በእኩል ነበር የጨረስነው። እናም ፉክክር ነበር በሁለታችንም መካከል ነበረ ።
ዘንድሮስ ?
” ዘንድሮ እንደ ቡድን አጀማመራችን ጥሩ አልነበረም። ግን አሁን እየተሻሻለ ሲመጣ ወደ ጎል እየቀረብን ነው። ይህንን ለማሻሻል እየሰራን ነው።
ከዛሬ ጨዋታ በፊት ክኮቪድ ጋር በተያያዘ  ቡድኑ  ስለነበረው ጫና ? 
” አዎ ከባድ ነበር። አሁን  አስቸጋሪ ነው። ኮቪድ ያለበት ወቅቱ አስቸጋሪ ነው ለእኛም ።
ኮቪድ ተይዟል ከተባለው 23 ተጨዋቾች ውስጥ ስለመኖሩ ?
” አዎ ነበርኩኝ።  ግን ደግሞ የተባለው  የኮቪድ ነገር  ትንሸ  ውሸት  ነው ብዬ ነው የማስበው ። ምክንያቱም እዚህ ከመጣን በኃላ ተመርምን ነበር ያንን አልተቀበልነውም ። ሁላችንም ላይ ትንሽ የእህምሮ ተፅኖ ፈጥሮብናል። ያም ይሁን ብለን ወደ አለማያ ዮኒቨርስቲ በማታ ተጉዘን  ተመርምረን ውጤቱ በመቀልበሡ ደስ ብሎናል።