ዜናዎች

“ከሁለት ቆንጆ ሴቶች አንዱን ምረጥ እንደማለት ነው ፤ ሁለቱም ውብ ናቸው“ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ

የ17ኛውን ሳምንት ጨዋታ በድል የተወጣው የባህርዳር ከተማ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ  አድርጓል።
ከሁለቱ ጎሎች የትኛውን ትመርጣለህ ለሚለው
“ከሁለት ቆንጆ ሴቶች አንዱን ምረጥ እንደማለት ነው ፤ ሁለቱም ውብ ናቸው። ስለዚህ ሁለቱም ቆንጆ ናቸው ።”
ጨዋታውን በተመለከተ እና በቀላሉ ጨዋታውን አሸንፈናል ብሎ ታስባለህ ለሚለው ?
“አልልም። የመጀመሪያው ጎል ለማስቆጠር ረጅም ደቂቃ ጠብቀናል ። መሀል ሜዳ ላይ በቁጥር አብዝተው ከጀርባ በሚጣሉ ኳሶች ሊያጠቁን እንደሚችል ከመጀመሪያው ገምተን ነበር ። ግን እኛ ደግሞ ሁል ጊዜ ስንጫወትበት በነበረው መንገድ ቶሎ ቶሎ ለማጥቃት ፈልገን በመጀመሪያ 45 አልተሳካልንም ።በሁለተኛው 45 ክፍተቶችን አግኝተናል ። ሙሉ ለሙሉ ተጠቅመናል ባልልም ያገኘናቸውን እድሎች ተጠቅመናል።ከባድ ጨዋታ ነበር በድሬዳዋ የመጀመሪያ ጨዋታችንን ማሸነፍ ለእኔም ለተጫዋቾቼም ጥሩ ነገር ነው”
በመጀመሪያው አጋማሽ በመልበሻ ክፍል ስለተወያዮት ነገር
“መጀመሪያ ልናጠቃ የነበረበትን መንገድ በቀላሉ ሲቆጣጠሩት ነበርና። በተለየ መንገድ አንዳንድ ክፍት ቦታዎች ይታዩ ነበር። ከውሳኔ ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው 45 እነሱን እየተጠቀምን አልነበርንም። አንድ ትክክለኛ ኳስ ባዬ ሲያገኝ ጎሉን አግብቷልና መጀመሪያው 45 ከነበርንበት የማጥቃት አካሄድ በሁለተኛው አጋማሽ ለመቀየር ሞክረናል”
በደረጃ ከፍ ስለማለታቸውና ዕቅዱ ?
“ረጅም ነው ጉዞዎ ። ገና ስምንት ጨዋታዎች ይቀሩናል ። ከፊታችን ፋሲል እያሸነፈ ነው። እኔ የምፈልገው በእያንዳንዱ ጨዋታ በአዕምሮም በአካልም ተዘጋጅተን ጨዋታዎችን ማሸነፍ ነው። ማሸነፍ ካለ መጨረሻ ወደምንፈልገበት ደረጃ እንደርሳለን ብለን እናስባለን። እስከአሁን የመጣንበትን መንገድ ተከትለን ለመጓዝ እንጥራለን።”