አትሌቲክስ ዜናዎች

የ50ኛው ዓመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል ! – ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል !

የ50ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓልን በማስመልከት የዘንድሮው ሻምፒዮናው ለየት ባለ መልኩ ዛሬ ይጀመራል። ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ያስጠሩ በርካታ አትሎቶች የሚታዮበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዘንድሮው በተለየ ዝግጅት  ደምቆ ዛሬ ይካሄዳል ተብሏል ። የዘንድሮው ሻምፒዮና  የአገሪቱ አብዛኞቹ ክለቦች ፣ ክልሎች እና ከተሞች የሚሳተፉ ሲሆን  በኮሮና ምክንያት ያለ ተመልካች የሚካሄድም እንደሆነም ተጠቁሟል ።
ዘንድሮ  ለ50ኛ ጊዜ  የሚካሄደው የኢትዮዽያ አትሌትክስ ሻንፒዮና በማስመልከት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ከቀናት በፊት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ላይ ለሽልማቱ ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበ ሲሆን የዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ የቡድንና የተናጥል አሸናፊዎች ከ10 ሺህ ብር እስከ 150 ሺህ ብር ሽልማቶች መዘጋጀቱን የውድድሩ አዘጋጆች በመግለጫቸው ማሳወቃቸው ይታወሳል።ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ አትሌቶች ብቻ ይሰጥ የነበረው የሽልማት አሰጣጥ በዘንድሮው ሻምፒዮና በማሻሻል ሽልማቱ እስከ 6ኛ ለወጡ አትሌቶች እንደሚሸለሙ ተጠቁሟል።
ዘንድሮ የሚካሄደው የኢትዮዽያ አትሌትክስ ሻንፒዮና በቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በOBN የሚተላለፍ መሆኑ ተጠቁሟል።