በስዊዘርላንድ ኑሯዋን ያደረገቸው እና በረጅም እና መካከለኛ ርቀቶች የግል ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በተደጋገሚ የምታሳተፈው አትሌት ሄለን በቀለ ትላንት በጄኔቭ የሲውዝ ኦሎፒክ ኮሚቴ ባዘጋጀው የማራቶን ውድድር ላይ አሸናፊ ሆናለች። አትሌቷ የትላንቱን የማራቶን ውድድር በ2 :24.57 በመግባት ማሸነፍ ችላለች።
አትሌት ሄለን በቀለ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም ከ ኢትዮጵያ ወደ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ከገባች በኋላ ኑሯዋን ከባለቤቷ አትሌት ተስፋዬ ኤቲካን ጋር በቋሚነት በስዊዘርላንድ በማድረግ እ.ኤ.አ. ከ2012 ለስዊዘርላንድ መወዳደር ጀመራለች ። የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ሄለን በ 2019 ዓ.ም በቶኪዮ ማራቶን ሁለተኛ ሆና የገባችበት ሰዓት ፈጣን ሰዓት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በተመሣሣይ የባርሴሎና ማራቶንን እና በሌሎች በርካታ የረጅም ርቀት ውድድሮችን አሸንፋለች ፡፡