የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከክፍለ ከተማ በሚገኘው ቄራ አልማዝዬ ሜዳ ዛሬ ረፋድ በመገኘት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር በመሆን ለቄራ አንበሳ ስፖርት ማህበር የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቄራ እና አካባቢው የሚኖሩ ባለሀብቶች በበኩላቸው የአልማዝዬ ሜዳን ከዲዛይን ጥናት ጀምሮ ሙሉ የሜዳውን ግንባታ ለማካሄድ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ለመቆም ቃል ገብተዋል ። በርካታ ስፖርተኞችን ያፈራው አልማዝዬ ሜዳ መሆኑን የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ በዘመናዊ መንገድ ግንባታው ይካሄዳል ብለዋል ። የትጥቅ ድጋፍ ዝግጅት ላይ ክከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ዋልያዎቹ በተጨማሪም የተለያዩ ባለሀብቶች እና አርቲስቶች ተገኝተ ዋል ።
ፎቶ ክአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት