ዜናዎች

ለዋልያዎቹ የተዘጋጀው ደማቅ አቀባበል እና ሽልማት ነገ ረፋድ ይቀጥላል !– የዛሬውን አዳር ጁፒተር ሆቴል ያሳልፋሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫን ከስምንት ዓመታት በኃላ ዳግም እንዲቀላቀል ያስቸለው ልዑካን ቡድን ከአቢጃን ኮትዲቯር በኢትዮዽያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላ አየር ተንስቶ ከአምስት ሰአት ተኩል በረራ በኃላ ምሽቱን ቦሌ የአየር ማረፊያ ደርሷል።
ከአርባ በላይ የብሔራዊ ቡድኑ ልዑካን ቡድን የያዘው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ምሽቱን ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ ዶ/ር ሂሩት ካሳ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር፣ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ፣የኢትዮጵያ አዠር መንገድ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ቁጥራቸው ቡዙም ያልሆነ  የብሔራዊ ቡድኑን መምጣት በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
በምሽቱ አጭር የአቀባበል ስነስርዓት ላይም በስፍራው የነበሩት እና ከቡድኑ ጋር ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳይያስ ጂራ ብሔራዊ ቡድኑ እና ዑካን ቡድኑን ወክለው አጭር የደስታ ንግግር አድርገዋል።ከምሽቱ የአቀባበል ስነስርዓቱም በኃላ ቡድኑ አዳሩን በጁፒተር ሆቴል ለማድረግ ወደ ተዘጋጀለት ሆቴል አቅንቷል።
በተያያዘ ዜና ከአቢጃኑ ድል በኃላ ምሽት አዲስ አበባ ለደረሰው እና ለአፍሪካ ዋንጫ ዋንጫ ለማለፍ ላበቃው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የጀግና አቀባበል መዘጋጀቱ ተሰምቷል። እንደመረጃው ከሆነ የነገ ረፋድ ዝግጅት ተጨዋቾቹ በክፍት መኪና ሆነው ከሚያጅባቸው ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እንደሚዘዋወሩ የተገለፀ ሲሆን ለጀግኖቹ ከፍተኛ የሽልማት የገንዘብ መታሰቡም መረጃው ይጠቁማል።