ዜናዎች

የዋልያዎቹን የዛሬ ጨዋታ ለመደገፍ 11 ኢትዮጵያዊያን ጉዞ ወደ አቢጃን ጀመሩ ! – ቴዲ አፍሮ ደጋፊዎቹ ወደ አቢጃን እንዲሄዱም ረድቷል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሁለተኛ ሆኖ ለማለፍ ዛሬ የመጨረሻውን እና ወሳኙን ፍልሚያ አቢጂያን ከኮትዲዮቫር አቻው ጋር በ10 :00 ሰዓት ያደርጋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ ለማለፍ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አልያም አቻ መውጣት እና አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ለማለፍ በቂው ነው።በአንፃሩ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲዮቫር ከተሸነፈደግሞ በምድቡ በመጨረሻ ደረጃ የምትገኘው እና መውደቋን ቀድማ ያረጋገጠችው ኒጀር ማዳጋስካርን ማሸነፍ ወይም ነጥብ የምታስጥልም ከሆነ ይሄም ለኢትዮጵያ ሌላው የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ መንገድ ነው።

 

በመጀመሪያው ጨዋታ 3 ለ 0 በማዳጋስካር በሜዳው ተሸንፎ የነበረው ኒጀር የዛሬውን የመልስ ጨዋታ በማዳጋስካር ሜዳ ላይ ለማሸነፍ እንደሚከብደው ቢገመትም : በእግርኳር ያልታሰበው ሊሆን ይችላልና በተመሣሣይ ሰአት የሚደረገውን ጨዋታው ተጠባቂም ያደርገዋል።ሌላው ምድቡን በ10 ነጥብ በመምራት ማለፏን ያረጋገጠችው ኮትዲዮቫር በባህር ዳር ሰታዲየም የደረሠበታን የ 2 ለ1 ሽንፈት ለመበቀል ብሎም የሽንፈቱን ታሪክ ለመስተካከል ለኢትዮጵያ ትልቅ ፈተና ልትሆን እንደምትችልም መገመት ይቻላል።ለኢትዮዽያጰ ብሔራዊ ቡድን በአቻ መለያየቱ በቂ ሲሆን አሁን ካለበት ዘጠኝ ነጥብ በአቻ ውጤት ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ይችላል። በተቃራኒው 7 ነጥብ ላለው ማዳጋስካር ተጋጣሚዋን ማሸነፍ እና የኢትዮጵያ መሸነፍን በመመኘት ላይ ብቻ ዕድሏ የተመሠረተው።

 

ተያያዘ ዜና የዛሬውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻውን ፍልሚያ ለመመልከት 11 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ወደ አቢጃን ከረፋዱ 4:30 ተጉዘዋል።የደጋፊዎቹ ወደ አቢጃን የሚያደርጉት ጉዞ አራት ሰአታት የሚፈጅ ሲሆን ከቀኑ ስምንት ሰአት ተኩል በአቢጃን የሚደርሱም ይሆናል። በአቢጃን ከደረሱም በኃላ ወደ ስታዲየሙ ለመድረስ የአንድ ሰአት ተኩል ጊዜ እንደሚፈጅ ተሰምቷል። ደጋፊዎቹ አቢጃን ከደረሱ በኃላ በተሳካ መልኩ ሰታዲየም እንዲደርሱ በስፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ሁሉንም ነገር እንዳመቻቹም ተሰምቷል።ከሁሉም በላይ ግን እነዚህ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች በስፍራው እንዲጓዙ ቴዲ አፍሮ የአየር መንገድ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸውን በማነጋገር እንዲተባበሩ በለስኬቱ ዋነኛውን ሚና የተጫወተው ሲሆን ደጋፊዎቹ ለቴዲ አፍሮ ምስጋናቸውን አቅርበዋል

One thought on “የዋልያዎቹን የዛሬ ጨዋታ ለመደገፍ 11 ኢትዮጵያዊያን ጉዞ ወደ አቢጃን ጀመሩ ! – ቴዲ አፍሮ ደጋፊዎቹ ወደ አቢጃን እንዲሄዱም ረድቷል!

Comments are closed.