አፍሪካ ዜናዎች

ሲዳማ ቡና የ36 አመቱን ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል ! – ተጨዋቹ ለብሔራዊ ቡድኑ ግዴታ ወደ ቤኒን ተጉዟል

በፈረንሣይ ቦርዶ የተወለደው እና ከ10 ክለቦች በላይ የተጫወተው ቤኒናዊው ፋቢየን ፋርኖል ለሲዳማ ቡና ፊርማውን  አካሄዶ ተጫዋቹ   ለብሔራዊ ቡድኑ ግዴታ ወደ ቤኒን ተጉዟል።በእግር ኳስ ህይወቱ ለበርካታ ክለቦች የተጫወተው እና እ.ኤ.አ በ2020 ለቱርክ ኢርዝሩምስፖር ክለብ ለመጫወት ፈርሞ ምንም ጨዋታ ያላደረገው ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ በቀሪዎቹ የውድድር ጊዜያት ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ተስማምቷል።

በፈረንሳይ በተወለደበት ቦርዶ  ከተማ ለሚገኘው እና በዋናው የፈረንሳይ ሊግ ለሚሳተፈው የቦርዶ ክለብን እ.ኤ.አ. ከ 2002 ዓ.ም ገና በ17 ዓመቱ የተቀላቀለ ሲሆን በክለቡ እስከ ኦ.ኤ.አ 2005 ለሦስት ዓመታት ያህል በ15 ጨዋታዎች ፋቢየን ፋርኖል  ተሰልፈዋል። በኃላም በ2005 የክረምቱ የክለቦች ዝውውር ተከትሎ ከፈረንሳይ ቦርዶ ወደ ፖርቱጋል በመቅናት ለፕሪሜራ ሊጋው ወገን ቪቶሪያ ዴ ሴቱባል ፈርሟል፡፡ ተጨዋቹ በክለቡ የአጭር ጊዜ ቆይታም ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ የመሆን ዕድል ለአንድ ዓመት አሳክቷል ።

ቤኒናዊው ፋቢየን ፋርኖል  እ.ኤ.አ እስከ  የካቲት 2015 ለስድስት ክለቦች ያህል ከተጫወተ በኃላ በ2015 ከሮማኒያው ክለብ ዲናሞ ቡካሬስት ጋር ለሶስት የውድድር ዘመናት ውል የተፈራረመ ቢሆንም በሊግ ካፕ ውስጥ አንድ ጨዋታ ብቻ በመጫወቱ እና የተጠባባቂ ወንበር በማሞቁ  ውሉን አፍርሶ ክለቡን በአመቱ ተሰናብቷል።
በኋላም እ.ኤ.አ. ከ2015- 2017 በፈረንሳዩ ሁለተኛ ሊግ የሚገኘው ሌ ሄቨር ኤሲ በመቀላቀል በ64 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፏል ።ከ2017 – 2020 ደግሞ በቱርክ ሊግ ለየኒ ማልታይስፖር እና ኢዝሩምስፖር በመጫወት አሳልፏል። ለቤኒን ብሔራዊ ቡድን እ.ኤ.አ ከ 2012 ጀምሮ እየተሰለፈ የሚገኘው ፋርናሌ የስምምነቱን ፊርማውን  ከሲዳማ ቡና ጋር ካኖረ በኃላ ለሀገሩ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ለመሰለፍ ወደ በቤኒን ተጉዟል፡፡
በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የፋቢየን ፋርኖል ቤኒን ነገ ናይጄሪያን በሜዳቸው ይገጥማሉ ። በምድብ “L” ቤኒን ከመሪዋ ናይጄሪያ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብላ በ7 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ፣ መሪዋ ናይጀሪያ በ8 ነጥብ ቀዳሚ ስትሆን ሴራሊዎንና ሌሴቶ በ3 እና 2 ነጥብ ስስተኛ እ
ና አራተኛ ጀረጃ ይዘዋል።