ዜናዎች

ከአሰልጣኝ ማሂር ዴቪስ በይፋ የተለያዩ ፈረሰኞቹ ቀሪውን የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ?

የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰፖርት ክለብ ከአራት ወራት በፊት ከጀርመናዊው ኤርነስት ሚድንዶርፕ ጋር መለያየታቸውን ይታወሳል። ክለቡ ከጀርመናዊው አሰልጣኝ ኤርነስት ስንብት በኃላ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴዎች ላይ እንደነበሩ ቢሰማም የውድድር ዓመቱ መጀመሩን ተከትሎ ከምክትል አሰልጣኙ ማሂየር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እሰከ 15ኛው ሳምንት አብረው የዘለቁ ቢሆንም ይፋዊ በሆነ መልኩ ከአሰልጣኝ ማሂየር ዴቪድስ ጋር ተለያይተዋል።
ፈረሰኞቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥር ሰባት ጨዋታ አሸንፈው ፣ በአምስቱ አቻ እና በሶስቱ ተሸንፈው በ26 ነጥብና በ 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም የቡድኑ ወጥ ያልሆነ ውጤት የክለቡ ኃላፊዎችንና ደጋፊውን ማስቆጣቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካዊው የ34 አመቱን አሰልጣኝ እንዲሰናበቱ አድርገዋል።
በምትኩም በቅርቡ የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ያደረጉትን የቀድሞ ተጨዋች ከአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሾመዋል። ፈረሰኞቹ  ቀሪውን የውድድር  ዓመት   ከአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ጋር  ይጨርሳሉ የሚለው  ነገር  እስካሁን እርግኛው  መረጃ አልታወቀም።አሰልጣኝ ደረጄ ተስፋዬ ደግሞ ወደ ተስፋ ቡድን እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል ። በተያያዘ ከቡድኑ ከዲሲፕሊን ቅጣት ጋር ከዋተናው ቡድን ታግዶ የነበረው የፈረሰኞቹ የቀድሞ ኮከቡ እና አንጋፋ አጥቂ ሳላዲን ሰይድ ልምምዱን አጠናክሮ ከዋናው ቡድን ጋር መቀጠሉ ታውቋል።