አትሌቲክስ

ኢትዮጵያን በቶኪዮ ፓራሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ተረጋገጡ!

አምስት አባላት ያካተተው የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን በቱንዚያ አገር አስተናጋጅነት እ ኤ አ ከማርች 14-21/2021 እየተካሄደ በሚገኘው የ2021 የቶክዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ የሚኒማ ማሟያ ( ማጣሪያ ) የውድድር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ። ከብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አንዱ የሆነው አትሌት ታምሩ ከፍያለው በ1500 ሜትር 03:56 በሆነ ሰዓት ውድድሩን ጨርሶ በመግባት ለቶኪዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያን የሚወክል መሆኑ ታውቃል ። በተጨማሪ አትሌት ያየሽ ጌቴ በሙሉ ለሙሉ አይነስውራን 200 ሜትር በአደረገችው ውድድር 28.99 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች ። በተመሳሳይ በዓይነ ስውራን ጭላንጭል በ1500 ሜትር በተደረገ ውድድር አትሌት ትግስት ገዘኸኝ ውድድሩን 4:31:53 በመግባት ውድድሩን አንደኛ በመሆን አጠናቃለች ። አትሌቶቹ ያስመዘገቡትን ሰዓት ተከትሎ ለ2021 ቶኪዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፋ ይሆናል ። በውድድሩ ወቅት ከፍተኛ ዝናብ እና ቅዝቃዜ የአየር ንብረት የነበረ በመሆኑ ውድድሩን ፈታኝ ቢያደርገውም አትሌቶቹ ዝናቡን እና ቅዝቃዜውን ተቋቁመው ውድድራቸውን በድል አጠናቀዋል ።