ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የ16ኛ ሳምንት የረፋድ ጨዋታ የነበረው የሐዋሳ ከተማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሆን በ1 ለ1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል።ጎሎቹን በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ጌታነህ ከበደ በሃዋሳ ከተማ በኩል ኤፍሬም አሻሞ አስቆጥረዋል።በውድድር አመቱ ሁለተኛውን ጎል ለሃዋሳ ከተማ በአቻነት ያስቆጠረው ኤፊሬም አሻሞ ጎሉን አስቆጥሮ ደስታውን የገለፀበት መንገድ በብዙዎች የተለየ ትርጓሜ መሠጠቱ እንዳሳዘነው ለኢትዮ ኪክ ይናገራል። ኢትዮኪክ :- የባህርዳር የመጨረሻ ጨዋታችሁ እንዴት ነበር ? ኤፍሬም :- የዛሬው ጨዋታ ከሞላ ጎደል ለማሸነፍ ነበረ ተነጋግረን የገባነው ። ግን አልሆነለሆነም ። ይሄም ውጤት ጥሩ ነው።ቀድሞ ጎል ቢቆጠርብንም ከዛ በⷛላ ተቆጣጥረን ለመውጣት ሞክረናል። ኢትዮኪክ :- የአቻነቷን ጎል አስቆጥረኃል ። ከጎሏ በኃላ በዳንስ ደስታህን ገልፀሃል : ስለ ዳንሱ ንገረኝ ? ኤፍሬም :- በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን በተመለከተ በፌስ ቡክ ላይ የማየው ነገር በጣም አሳዝኖኛል።አንዳንድ ሰዎች በፌስቡክ ላይ የተሳሳተ ትርጓሜ እና የወሰዱበት መንገድ እንዲሁም የሚሰጡት ሃሳብ በጣም ስህተት ነው። የደነስኩት ካስተዋላችሁ ሁለት ጊዜ ነው። እኔ ጎል ካገባሁ በኃላ ድሮም የማድረገው ነው ያደረኩት። ሰዎች ወደሌላ መንገድ ወስደውት ሳይ በጣም ነው ያዘንኩት ።ኢትዮኪክ :- በፌስቡክ ነው ወይስ በአካል የሰዎች አስተያቶች የገጠሙህ ? ኤፍሬም :- በፌስቡክ ላይ ነው ያየሁተ። ሰዎች የወሰዱበት መንገድ ትክክል አይደለም። እንዳልኩት ከድሮም ጀምሮ ጎል አግብቼ እደንሳለሁ። ድሮ የማደርገውን ነገር ነው ያደረኩት። የተለየ ነገር አይደለም ።ሰው የተረዳበት መንገድ ስህተት ነው። ኢትዮኪክ :- በዚህስ ምክንያት ኤፍሬም ከዚህ ቀኃላ ጎል አስቆጥሮ መደነሱን ይተዋል ? ኤፍሬም :- ሰዎች በመጥፎ ነገር እንዳያሳቡትና እንዳይተረጉመው እፈልጋለሁ። ግን በዚህ የተነሣ መደነሰን አላቆምም። አሁንም ደስታዬን ከመግለፅ ወደⷛላ አልልም። ኢቶዮኪክ :- ኤፍሬም ከሃዋሳ ጋር የሚያስበው ነገር ይኖር ይሆንኤፍሬም :- ከእመቤቴ ጋር ጥሩ ጊዜን አሠሳልፌለው ብዬ አስባለሁ።