አፍሪካ ዜናዎች

ሀዲያ ሆሳዕና የፊታችን ሀሙስ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራል !

👇
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት በጠንካራ ተፎካካሪነት በስምንተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የሀዲያ ሆሳዕና ስፖርት ክለብ በቀጣይ አመት የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ እና የክለቡን የፋይናንስ አቅሙን የበለጠ ለማጠናከር ለወዳጅነት ጨዋታ እና ለገቢ ማሰባሰቢያ ወደ ፕሪቶሪያ የፊታችን ሀሙስ ያመራል።
ነብሮቹ የፊታችን ሀሙስ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም በማምራት በደቡብ አፍሪካ ናሽናል ዲቪዢን ላይ ተሳታፊ ከሆነው ጂ ዲ አር ስታር ከተባለው ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታቸውን እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የሚያደርጉ ሲሆን በመቀጠል የገቢ ማሰባሰብ በዚሁ ጉዞ ላይ ይኖራል.
በጉዞ ዙሪያ ላይ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የክለቡ የበላይ ጠበቃ የሆኑት አቶ ማቲዮስ አኒዮ እና የዞኑ ምክትል አስተዳደሪና የክለቡ ፕሬዝዳንት ከቦርድ አመራሮች ጋር በጉዞ ዙሪያ ላይ ግምገማ በማድረግ በመጨረሻም መግለጫ ሰጥተዋል ።
በዚህ መሠረት ነብሮቹ አስፈላጊውን ሁሉ በማጠናቀቅ ወደ ፕሪቶሪያ ያቀናሉ. የዚህ አይነቱ የወዳጅነት ጨዋታ በክለቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ ከመስጡቱም በላይ ለተጫዋቾች እና ለአሰልጣኞች የኢንተርናሽናል የጨዋታ ልምድ የሚያገኙበት አጋጣሚ ይፈጥራል.
የክለቡ ተጫዋቾች በተለያዪ መልኩ በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው በጨዋታው ላይ እንዲገኙም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል.
May be an image of 4 people, people playing soccer and people playing football