ከቀናት በፊት የስዊውዲኑን ዋናው ሊግ የሚወዳደረውን Djurgårdens IF የ16 ዓመቱን ድንቅ ብቃት ያለውን ትውለደ ኢትዮጵያዊ ኢይሳክ አሌክሳንደር አለማየሁ ማስፈረሙ ተዘግቦ ነበር።
የስዊድን ዋናው ሊግን 12 ጊዜ ዋንጫ የበላው እና በአውሮፓ ማህበረሰብ እና ቻምፒየንስ ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው DIF ክለብ ታዳጊውን ወደዋናው ቡድን አሳድጓል።
(እ.ኤ.አ. 2006) በስዊድን የተወለደው ኢይሳክ አሌክሳንደር ከኒውካስትሉ ኤርትራዊ አሌክሳንደር ኢይሳክ ጋር በስም ሞክሼ ይሁን እንጂ የዚህ ታዳጊ አባቱ አቶ አለማየሁ ሙልጌታ እንዲሁም መላው የአባቱ ቤተሰቦች ከለምለሚቱ ኢትዮጵያ በወላይታ ዞን ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በአገር እና በውጭ የሚኖሩ ሲሆኑ የኢትዮጵያን እና የክልሉን ስፖርት ለማሳደግ ጥረት ከሚያደርጉ ከስፖርት ጋር ግንኙነት ካለቸው ቤተሰብ የተገኘ ታዳጊ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የ16 ዓመቱ አማካይ አይዛክ አሌክሳንደር ለስዊድኑ ታዋቂ ክለብ DIF ዋናው ክለብ ከመፈረሙ በፊት በታዳጊዎች አካዳሚ በነበረበት ጊዜ ጠንካራ ብቃቱን በማሳየቱ ከፍተኛ ትኩረት ማግኘት ችሏል ። ታዳጊው ከዚህ በተጨማሪም በሲውዲን ታዲጊ ቡድን የመመረጥም ዕድል አግኝቶ ነበር።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ አይዛክ አሌክሳንደር በዋናው ቡድን በዕድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኖ እስከ 2025(እ.ኤ.አ) ለቀጣዮቹ ዓመታት በአማካኝ ስፍራ ለመጫወት DIF ፈርሟል።