Kenenisa2021
አትሌቲክስ ዜናዎች

ጀግኛው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የበርሊን ማራቶን ላይ ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅቷል!!

ተጠባቂው የበርሊን ማራቶን መስከረም 16/ 2014 ይካሄዳል። የ39 አመቱ ቀነኒሳ በቀለን እእአ ከ2019 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ሀጂ አዴሎ የቀነኒሳን ብቃት ከባለፈው የበርሊን ማራቶን ጋር አነጻጽረው አሁን በጣም በተሻለ ብቃት ላይ እንደሆነና ክብረ ወሰን ለማሻሻልም የሚያስችል አቋም ላይ እንደሆነ ተናግረዋል። ቀነኒሳ እእአ በ2019 በተካፈለበት ማራቶን በኬኒያዊው ኢሉድ ኪፕቾጊ የተያዘዉን ክብረወሰን ለጥቂት (ለሁለት ሰከንድ) ሳይሰብረው መቅረቱ የሚታውስ ነው።
ቀነኒሳ ከ18 ወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የተካፈለበትን የለንደን ግማሽ ማራቶን ካሸነፈ በኋላ ምንም አይነት ውድድር አልተሳተፈም፣ ይህም ቀነኒሳ ውድድር ሳይካፈል የቆየበት ረጅሙ ጊዜ ያደርገዋል። ቀነኒሳ ከበርሊን ማራቶን በማስከተል ከ42 ቀናት በኋላ በነውዮርክ ማራቶን ለመካፈል እቅድ ይዟል።
“ለሁለት አመታ ያህል ውድድር አለመሳተፍ እንደ አትሌት በጣም ይከብዳል” ያለው ቅነኒሳ አክሎም “ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም የትድረስ መሄድ እንደሚቻል ማየት ፈልጋልሁ።” በማለት ለስፖርት ኢሉስትሬተር ተናግሯል።
በውድድሩ ከቅነኒሳ በተጨማሪ ጉዪ አዶላ፣ ታዱ አባተ እና ኦሊካ አዱኛ ከኢትዮጵያ የሚሲሳተፉ ይሆናል። በሴቶች ሂወት ገብረኪዳን ለውድድሩ ከፍተኛ ግምት የተሰጣት አትሌት ስትሆን ብሪሾ አማን፣ ሱሬ ደምሴ እና ቤተልሄም ሞገስ ከኢትዮጵያ የሚሲሳተፉ ይሆናል።