ዜናዎች

ኤርትራ በቡሩንዲ ሽንፈትን አስተናግዳለች!

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ በመክፈቻው ጨዋታ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በሦስት እኩል አቻ የጀመሩት የኤርትራ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከቡሩንዲ አቻቸው ባደረገው ጨዋታ የ3 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
በትላንቱ የከባድ ዝናብ ምከንያት የሁለተኛው አጋማሽ የተቋረጠው እና ዛሬ ረፋድ በቀጠለው ጨዋታ የቡሩንዲ ታዳጊ ቡድ ን በዛሬው ጨዋታ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር በአጠቃላይ ውጤት 3 ለ 0 የኤርትራ ብሔራዊ ቡድንን አሸንፏል። ለቡረንዲ ብሔራዊ ቡድን ጎሎቹን በትላንቱ ጨዋታ በ15ኛው ደቂቃ በቅጣት ምት ንሺሚሪማና ይስማዕ ሲሆን በዛሬው ጨዋታ በ53 ኛው ደቂቃ ሩኩንዶ አብዱራህማኒ እንዲሁም በ83 ኛው ደቂቃ ሃኪዚማና ኢሳ በማስቆጠር ኤርትራን አሸንፈው ወጥተዋል።
እንደሚታወሰው የኤርትራው ዓሊ ሱሊማን በሶስት ጎሎች የሴካፋ የጎል መሪነቱን በቀዳሚነት ይዞ ይገኛል።
Pic @EFF