ዜናዎች

🛑 ብሔራዊ ቡድኑ ለጊኒ ጨዋታ 23 ተጫዋቾች ይፋ ሆነዋል- ነገ ማለዳ ወደ ጊኒ ቢሳው ያመራል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች የሚያደርገውን የአዲስ አበባ  ዝግጅት  ጨርሰዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ቢሳው እና ጅቡቲ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ከቀናት በፊት ዝግጅታቸውን  የጀመሩት ዋልያዎቹ  የአዲስ አበባ  ዝግጅት  ጨርሰው ብሔራዊ ቡድኑ ነገ  ማለዳ 2:35  ወደ ጊኒ ቢሳው የሚያመራ ሲሆን በመጪው ሐሙስ ከጊኒ ቢሳው አቻው ጋር ቢሳው ከተማ ላይ ጨዋታውን ያደርጋል

 

አሰልጣኙ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾች ዝርዝር

👇

 

ግብ ጠባቂዎች:-

ሰይድ ሀበታሙ ፣ ፍሬው ጌታሁን እና አቡበከር ኑራ

ተከላካይ:- 

ጊት ጋትኩት ፣ ብርሀኑ በቀለ ፣ ፍሬዘር ካሳ ፣ ሚልዮን ሰለሞን ፣ ፈቱዲን ጀማል ፣ ፍቅሩ አለማየሁ ፣ ረመዳን ዩሱፍ እና ያሬድ ካሳዬ

አማካይ :-

ስፍራ ጋቶች ፓኖም ፣ ብሩክ ማርቆስ ፣ ወገኔ ገዛኸኝ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ ፣ ፉአድ ፈረጃ ፣ ቢንያም በላይ ፣ አብነት ደምሴ እና ቢንያን አይተን

አጥቂ :- 

ከነአን ማርክነህ ፣ ቢንያም ፍቅሩ ፣ መስፍን ታፈሰ እና ምንይሉ ወንድሙ

ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ወደ ቢሳው የሚያመራ ሲሆን በመጪው ሐሙስ ከጊኒ ቢሳው አቻው ጋር ቢሳው ከተማ ላይ ጨዋታውን ያደርጋል