አትሌቲክስ

🏆አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተባለ ! 

 

 

ኢኤስፒኤን (ESPN) የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ አድርጓል፡፡

 

ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሁለት ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

 

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

 

በሴቶች የዚምቧብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ መቻሏን መረጃው ያመላክታል።