ዜናዎች

⭕ የዋልያዎቹ አጥቂ አቡበከር ናስር ከጉዳቱ ለማገገም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መሆኑን አሰልጣኙ ይፋ አድርገዋል!

 

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  የፊት መስመር  ተጨዋቾች  አቡበከር ናስር በክለቡ የደቡብ አፍሪካው ቻምፒዮንስ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ያጋጠመው ጉዳት የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ኮከብ አቡበከር ናስርን ህይወት እያወዛገበ መሆኑን ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ተናግረዋል።

እንደ አሰልጣኙ መረጃ አቡበከር ናስር ባለፈው አመት June ወር በኦርላንዶ ፓይሬትስ ግብ ጠባቂ ሲያቦንጋ ምፖንትሻን ባጋጠመው አስደንጋጭ ጉዳት ምክንያት
ከጉዳት ለማገገም እስካሁን እየታገለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

 

አሰልጣኙ እንዳሉት ጉዳቱ ትንሽ አሳዛኝ እና ለእግርኳስ ህይወቱ አስጊ ይመስላል ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ ከደቡብ አፍሪካ ከሚወጡ መረጃዎች አቡበከር ከጉዳቱ ጋር በክለቡ ያለው ቀጣይ ቆይታ አስጊ መሆኑን ቢዘግቡም አሰልጣኙ ግን አቡበከር ናስር ትልቅ ድጋፍ ያስፈልገዋል ለዚህም ትክክለኛው ቦታ ላይ ነው ያለው በቅርብ እንደምንመለከተው ተስፋ አለን ሲሉ ተደምጠዋል።

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ከአቡበከር ናስር ጋር በተያያዘ ያለወን ወቅታዊ መረጃ አስመልክተው በቅርቡ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።