👇
በተጠናቀቀው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው እና በዘንድሮ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር ላይ የዋንጫ ፍልሚያ ላይ የደረሰው የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ጀምሯል.
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ወላይታ ድቻ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጎልቶ የወጣውን አጥቂ ቢንያም ፍቅሬ በግብፅ ክለቦች ተፈልጎ በአሁን ሰአት ካይሮ እንደሚገኝ ሲታወቅ ተጨዋቹ በግብፁ እስማኤሊያ አልያም የቀድሞ የሽመልስ በቀለ ክለብ አል ኢታሀድ ጋር ስምምነት ሊያደርግ እንደሚችል ታውቋል.
በሌላ በኩል ወላይታ ድቻ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ ገበያ በመግባት ሦስት ተጨዋችችን አስፈርሟል. የፈረሙት የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾቹ ሙሉቀን አዲሱ እና ቴዎድሮስ ታፈሰ እንዲሁም ተከላካዩ ውብሸት ክፍሌን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረማቸውን ሲታወቅ የአማካዩ መሳይ ኒኮል እና የተከላካዩ አዛሪያስ አቤልን ደግሞ ውላቸውን ማርዘማቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ።