ዜናዎች

⭕የዲሲ ዩናይትድ ክለብ አመራሮች እና የኢ.እ.ፌ ጉዳዮች

 

 

🕳 ብሔራዊ ቡድኑ ወደ አሜሪካ አምርቶ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል
🕳ሱራፌል ዳኛቸው ወደ ዲሲ ያቀናል
🕳 የሸገር ደርቢ ጨዋታ ዲሲ ላይ ሐምሌ 12 ያከናውናል
🕳የዲሲ ዩናይትድ አመራሮች የካፍ ልህቀት ማዕከልን ጎብኝተዋል
👇
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር በዛሬው ዕለት በጋራ ለመስራት ይፋዊ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን መዘገባችን ይታወሳል።
– በዛሬው መርሐ ግብር ላይ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የኢ/እ/ፌ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ አቶ ኢዮብ ማሞ፣ ሚር. ጄሰን ፣ አቶ ማርቆስ ፣ አቶ ነብዩ እና ሌሎች የዲሲ ዩናይትድ ክለብ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/ማ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለብ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አምርቶ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል።
– ሱራፌል ዳኛቸው ወደ ዲሲ ዩናይትድ መጋቢ ክለብ ሎውዶን ዩናይትድ ያመራበት ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።
– ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢ ጨዋታ በዋሺንግተን ዲሲ ሐምሌ 12 ያከናውናሉ።
– የዲሲ ዩናይትድ ባለድርሻዎች እና አመራሮች በዛሬው ዕለት ከተካሄደው ስነ ስርዓት አስቀድሞ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍ ልህቀት ማዕከል ተገኝተው በማዕከሉ ያሉ የስሪ ፖይንት አካዳሚን ጎብኝተዋል።