ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

⭕የኢትዮጵያ ቡናው ሰርቢያዊው አሰልጣኝ የመመለስ ነገር?

የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ዋና አሰልጣኝ የ48 ዓመቱ ሰርቢያዊ ኒኮላስ ካቫዞቪች የ5ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን ካደረጉ በኃላ ከጤና እና ከግል ጉዳያቸው ጋር በተያያዘ የዕረፍት ጊዚያቸውን በመጠቀም ወደ ሀገራቸው ሰርቢያ እንደሚሄዱ አሳውቀው ተሰናብተዋል።
አሰልጣኙ ከቀናት በፊት የክለቡ አመራሮች ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ እያደረጉ እንዳልሆነ የሚያሳይ ንግግር ከተናገሩ በኋላ ከአመራሮቹ ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሲታወቅ ንግግራቸውን አስመልክተው ክለቡንና ደጋፊዎችን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።
ክለቡ ከቀናት በፊት እንዳስታወቀው አሰልጣኙ ሰርቢያ ነገሮችን አስተካክለው የሊጉ የዕረፍት ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ቡድናቸውን የሚቀላቀሉ ይሆናል ብሏል።ነገር ግን አሰልጣኝ ኒኮላስ ካቫዞቪች ተመልሰው የመምጣታቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑን የሚያሳይ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል።