አፍሪካ ዜናዎች

⭕ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና አልቢትር ባምላክ ተሰማ በአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፉ ጨዋታ ዛሬና ነገ ተሰይመዋል!

👇

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ብሔራዊ ቡድኗ ባይሳተፍም ኢትዮዽያን ወክለው ግን ሦስት ባለሙያዎች የሀገራችንን ስሟን በመልካም እያስጠሩ ይገኛል።

ከነዚህ ባለሙያዎች መካከል የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና ስሙ በተለያዩ ሚዲያዎች በድንቅ የዳኝነት ውሳኔው እየተሞገሰ ያለው አልቢትር ባምላክ ተሰማ ናቸው።

የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የአፍሪካ ዋንጫው ቴክኒካል ጥናት ቡድን አባል በመሆን ውድድሩ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ተሰይሞ ታይቷል።
በተመሳሳይ ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ በዚሁ የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በመሐል ዳኝነት እና በአራተኛ ዳኝነት ላይ የዳበረ ልምዱን በፈገግታ ተሞልቶ እያሳየም ይገኛል።

ከዚሁ ጋር ሁለቱ ባለሙያዎች የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት አንጎላ ከ ናሚቢያ በሚያደርጉትን ጨዋታ ላይ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የቴክኒክ ጥናት ክፍል ኢትዮጵያን ወክሎ በሙያው የሚታደም ይሆናል።

በተመሳሳይ ነገ 2 :00 ሰዓት ምሽት ኢኳቶሪያል ጊኒ ከ ጊኒ የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ በረዳት አራተኛ ዳኛ ሆኖ በሙያው የሚታደም ይሆናል።
የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ የፍፃሜ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት እንዲመራ ፍላጎቶች መጨመራቸውን ተዘግቧል።

በተያያዘ ኮሚሽነር ተስፋነሽ ወረታ በካፍ የዳኞች ኮሚቴ አባል በመሆን በውድድሩ ላይ ተሳትፎ እያጀረገች ነው ። እንደሚታወቀው ተስፋነሽ በካፍ ኮሚሽነርነት እየሰሩ ከሚገኙ አራት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አንዷ ናት።