ዜናዎች

⭕ሱሬፌል ወደ አሜሪካ ሊግ ሊያቀና ነው!

የፋሲል ከነማው አማካይ ሱራፌል ዳኛቸው ወደ አሜሪካ ሊያቀና መሆኑ ዛሬ ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4 ለ 2 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ ተሠምቷል።
ይህን ተከትሎም በጉዳት ላይ የነበረው ሱራፌል የዛሬውን ጨዋታ ከሜዳ ውጭ ተመልካች ሆኖ ጨዋታውን ሲመለከት ተስተውሏል።
የሱፐርስፖርት የጨዋታ ከሜንታተሮች ሰይድ እና ዮናስ የቀጥታ ስርጭት መረጃ ሱራፌል ወደ አሜሪካ በቀጣይ ቀናቶች ሊያቀና መሆኑን ተገልጿል።
በተለይ እንደ ጋዜጠኛ ዮናስ ኣዘዘ መረጃ መሠረት በሁለተኛው ዙር ጨዋታ ሱራፌል ከዓፄዎቹ ጋር እንደማይኖር እና ወደ ኣሜሪካ ሊግ የሚያረገውን ዝውውር መጨረሱን ይፋ አድርጓል። ይሁንና ሱራፌል የአሜሪካው የትኛው ሊግ እና ክለብ እንደሚዘዋወር አልተገለጸም።