አሰልጣኝ ስዩም ከኮቪድ የምርመራ ውጤት እና ከነበረባቸው በስታዲየም ያለመገኘት ገደብ ጨርሰው ከቡድናቸው ጋር በ20ኛው ሳምንት ጨዋታ ተገኝተው ጨዋታው ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር 1 ለ 1 በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።
በ20ኛው ሳምንት በአጠቃላይ 12 ጎሎች ከመረብ ተዋህደዋል። በብዛት ጎሎች ተቆጥረውበት ጨዋታ ሰበታ ከወላይታ ድቻ ጨዋታ ሲሆን 2 ለ 2 የተጠናቀቀው ጨዋታ ነው። በ20ኛው ሳምንት 3 ጨዋታዎች 1 ለ 1 አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለት ጨዋታ 1 ለ 0 የተጠናቀቀ ነው።
በ20ኛው ሳምንት ፈጣን ጎል ያስቆጠረው የጅማ አባጅፋሩ ተመስገን ደረሰ ሲሆን ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ 46ኛው ደቂቃ ባልሞላ ግማሽ ሰከንድ ጊዜ ውስጥ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አቻ የሚያደርጋቸውን ጎል ተመስገን አስቆጥሯል። የተመስገን ለሁለተኛ ጊዜ በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ፈጣኗን ጎል ሲያስቆጥር በአጠቃላይ ያስቆጠራቸውን የጎሎች ብዛት ስድስት አድርሷል።
በ20ኛው ሳምንት ወልቂጤ ከተማዎች በረመዳን የሱፍ ጎል አሸንፈው ሊወጡ የነበራቸው ተስፋ ጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ለአዳማ ከተማ ተቀይሮ በገባው በላይ አባይነህ አማካይነት አቻ በመሆናቸው የወልቂጤ ከተማ ተጨዋቾች ሃዘናቸውን በስታዲየም ክፉኛም ሲገልፁ ተስተውሏል።
በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በ20ኛው ሳምንት ወጣት እና ተስፋ የሚጣልባቸው ተጨዋቾች ጎሎች ያስቆጠሩበት ሳምንት ነበር ማለት ይቻላል።
ከእነዚህም መካከል
ቸርነት ጉግሳ – ወላይታ ድቻ
ወንድማገኝ ሃይሉ – ሐዋሳ ከተማ
አለማየሁ ሙለታ – ሰበታ ከተማ
ሙኅዲን ሙሳ – ድሬዳዋ ከተማ
ረመዳን የሱፍ – ወልቂጤ ከተማ
ፀጋሰው ድማሙ -ሀዲያ ሆሳዕና
ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ጨምሮ በ20ኛው ሳምንት ከአራት በላይ ክለቦች በምክትል አሰልጣኝ ተወክለው ታይተዋል።
በ20ኛው ሳምንት ብዙ የማስጠንቀቂያ ካርድ ያልታየበት ሳምንት ሆኖም አልፏል። የፋሲል ከነማው ሱራፌል ዳኛቸው የ5 ቢጫ ካርድን ለሁለተኛ ጊዜም በማየት የአንድ ጨዋታ እና 1500 ብር ቅጣት አስተናግዷል።ሱራፌል በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 10 ቢጫ ካርድ በማየት ቀዳሚም ሆኗል።
በ20ኛው ሳምንት የባህርዳሩ ባዪ ገዛኸኝ እና የሐዋሳው ምኞት ደበበ በአምስት ቢጫ ካርድ የ1500ሺህ ብር ቅጣት እና አንድ ጨዋታ የማይሰለፉም ይሆናል
በ20ኛው ሳምንት ከፍተኛ ጎል አሰቆጣሪነቱን
አቡበከር ናስር ➖ የኢትዮ.ቡና (22 ጎሎች)
ሙጂብ ቃሲም ➖ ፋሲል ከነማ (18 ጎሎች )
ጌታነህ ከበደ ➖ ቅዱስ ጊዮርጊስ(12 ጎሎች