ዜናዎች

➖◾ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አስገራሚው አጋጣሚዎች – እውነታዎች ◾➖

➖⚽ቤትኪንግ ፕሪምየር አስገራሚው አጋጣሚዎች በ19ኛው  ሳምንትም ታይትዋል ። በ19ኛው ሳምንት በአጠቃላይ 16 ኳሶች ከመረብ ተዋህደዋል።
በብዛት ጎሎች ተቆጥረውበት የተጠናቀቀው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ከሃዋሳ ከተማ ያደረጉት ሲሆን ሃዋሳ 3 ለ 2 አሸንፏል።
➖⚽ የሰበታ ከተማው ኦስይ ማወሊ የ19ኛው ሳምንት ሁለት ጎሎች ያስቆጠረ ብቸኛው ተጨዋች ነው።
➖⚽በ19ኛው ሳምንት ፈጣን ጎል ያስቆጠረው ሙጂብ ቃሲም ሲሆን በ3ኛው ደቂቃ ቡድኑ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፎ በወጣበት ጨዋታ ነው።
➖⚽  ወላይታ ድቻ እና ሃዋሳ ከተማ ተቀያሪ ተጨዋቾች ሳይኖራቸው ግብ ጠባቂን ገልብጠው አጥቂ ቦታ ማሰለፍ ተገደዋል። በተለይ በወላይታ ድቻ በኩል ሁለቱ ግብ ጠባቂዎች መክብብ እና አብነት በጨዋታው በአጥቂ ቦታ ተሰልፈዋል የግብ ሙከራዎችም ሲያደርጉ ተስተውሏል ። በሁለቱም በኩል ተቀያሪ ተጨዋቾች የሌሉበት የመጀመሪያው የቤትኪንግ ሊግ ጨዋታም ሆኗል። ለተጨዋቾች ያለመኖር በዋነኝነት ኮቪድ ትልቁን ቦታ ይዟል ።
➖⚽ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ከቡድናቸው ጋር  በ19ኛው ሳምንት በጨዋታው ሜዳ አልተገኙም በጨዋታው ሜዳ ምክትል አሰልጣኙ አብዱልሀኒ ተሰማ እየተመሩ በሀዲያ ሆሳዕናን ገጥመው 2 ለ0 ሽንፈት አስተናግደዋል።
➖⚽ባህርዳር ከተማም በ19ኛው ሳምንት ምክትል አሰልጣኝ ታደሰ ጥላሁን ወደ ሜዳ የገባው ። አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ከድሬ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በሜዳ አልተገኙም።
➖⚽ከኮቪዲ ምርመራ ጋር የሚሰማው አወዛጋቢው የምርመራ ውጤት በ19ኛው ሳምንትም ቀጥሏል። ከቀናት በፊት በድሬደዋ ምርመራ ውጤት ኮቪድ ተገኘባችሁ የተባሉት 18 ዳኞች በሀረማያ ዩኒቨርስቲ የምርመራ ውጤታቸው መሠረት አስራ ሰባቱ ነፃ ናችሁ ተብለዋል።
➖⚽ ሸገር ደርቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ በድሬደዋ ተካሄዶ አስቻለው ታመነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አስገራሚ ጎል በማስቆጠር 1 ለ0 የተጠናቀውም በ19ኛው ሳምንት ነበር።