ዜናዎች

➖በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ላይ የሰዓት ለውጥ ተደረገ!

የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከቀናቶች መቋረጥ በኃላ የፊታችን እሁድ ህዳር 12 በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከአራተኛው ሳምንት እስከ ዘጠነኛው ሳምንት የሚቀጥል ይሆናል።

በወጣው መረጃ መሠረትም በቀጣይ ሳምንታት የሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ የሰዓት እና የደጋፊዎች የስታዲየም አገባብ ላይ ለውጥ ተደርጓል።

በዚህ መሠረት ከህዳር 12 እስከ ታህሳስ 15/2014 ዓ.ም ባሉ ቀናት ውስጥ የሚካሄዱት የቅዳሜ እና የእሁድ ጨዋታዎች የሰዓት ለውጥ የተደረገ ሲሆን በፊት ይካሄድ የነበረው የቅዳሜና እሁድ የስምንት ሰዓት ጨዋታዎች በቀጣይ መርሐ ግብር በዘጠኝ ሰዓት የሚካሄዱ ሲሆን እና ሁለተኛው ጨዋታ በ12፡00 ሰዓት የሚቀጥል ይሆናል።


በተያያዘም በሁሉም ጨዋታዎች የኮቪድ ፕሮቶኮሉ ተጠብቆ የሃዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ለደጋፊዎች ክፍት ሲሆን ማንኛውም ተመልካች ወደ ስታዲየም ሲመጣ ከመግቢያ ትኬት በተጨማሪ ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ እንደሚኖርበትም ይኸው መረጃው ያመለክታል ። የስታዲየም መግቢያ ትኬት ባለሜዳ ክለቦች በሚያመቻቹት መንገድ የሚሸጥ እንደሆነም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ መረጃ ያመለክታል።