ዜናዎች

ፋሲል ከነማ የወዳጅነት ጨዋታ ከእስራኤል ክለብ ግብዣ ቀረበለት!

የቅ/ጊዮርጊስ እና የቡና ሁለት ተጨዋቾች በድብይ ክለብ የሙከራ ዕድል አግኝተዋል

 

 

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ የውድድር ዓመቱን ከመጀመራቸው በፊት በ2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ የብሔራዊ ቡድኑ አብዛኞቹን ተጨዋቾችን በማስፈረም ቀዳሚ መሆናቸው ይታወሳል።

ፋሲል ከነማዎች የውድድር ዓመቱን በድል ከጀመሩ በኋላም በአንደኛው ዙር በ15 ጨዋታዎች ስድስት አሸንፈው በአምስቱ አቻ ወጥተው በአራቱ ደግሞ ሽንፈን አስተናገደው በአምስተኛ ደረጃ አጠናቀውም ነበረ።
ዓፄዎቹ የ2016 የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛው ዙር ከሳምንት በፊት ከመቀጠሉ በፊት ደግሞ ከ2011 እስከ 2016 አመት ያገለገለው ቁልፍ ተጨዋቻቸው ሱራፌል ዳኛቸው ለአሜሪካው ዲሲ ዩናይትድ ስፖርት ክለብ ፈረሙን ተከትሎ መለያየታቸው አይዘነጋም

ይሁንና አሰልጣኝ ውበቱ የሚመራው የፋሲል ከነማ ቡድን ሁለተኛ ዙር የውድድር ዓመትን በ2 ለ 1 ውጤት በመጀመር ቡድናቸው በዘንድሮው የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ያሰቡትን ለማሳካት  የቀጠሉ ይመስላል።

በአንፃሩ ለኢትዮኪክ በደረሷት ታማኝ መረጃዎች መሠረት የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከእስራኤል ሊግ ከሚጫወት ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ጥያቄ እንደቀረበለት እና ጊዜው ሲደርስ ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ መረጃው ያመለክታል።

እንደመረጃው ከሆነ የፋሲል ከነማ ክለብ ጉዞውን የሚያደርገው የውድድር ዓመት ሲጠናቀቅ በመጪው የክረምት ወራት ሲሆን በተመሣሣይ ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓፄዎቹ ወደ እስራኤል የሚጓዙ መሆኑን የኢትዮኪክ ታማኝ መረጃ አሳውቋል።

በተያያዘ ዜና ከሳምንታት በፊት የሸገር ደርቢን ዱባይ ላይ ያደረጉት ከቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ እና ከኢትዮጵያ ቡና አንድ አንድ ተጨዋች ለሙከራ ወደ ከድባዮ ሽበላሌ የተባለ ክለብ ጋር ለያደርጉ መሆኑ ተሰምቷል።

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች በሚወጡ ሰዓት እናደርሳለን