ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ፈረሰኞቹ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልምምድ ስፍራና ሆስቴል ግንባታ መሬት ባለቤትነት በዛሬው ዕለት በይፋ ተረከቡ!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም በወሰነው ውሳኔ መሠረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የልምምድና የተጫዋቾች ማረፊያ ሆስቴል ግንባታ ቦታ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፤ በመሆኑም ክለቡ አስፈላጊውን የሊዝ ውል በመፈፀም እና ለይዞታውም በ20/05/2012 ዓ.ም. ካርታ በማግኘት ጭምር ቦታውን ለማልማት የተለያዩ ጥረቶች ያደረገ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት ቆይቷል። በተለይም በይዞታው ላይ 3 የይገባኛል ክሶች ቀረበው ከሁለት ዓመታት በላይ ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ፍርድ ቤቶቹ ይዞታው ለቅዱስ ጊዮርጊስ በህግ አግባብ የተሰጡ መሆናቸውን በማረጋገጥ ውሳኔ እስኪሰጡ ድረስ የፈጀው ጊዜ ጉዳዩን ካጓተቱት ምክንያቶች መካከል ዋንኛው ነበር፡፡
በአሁኑ ወቅት ግን አስፈላጊ ሁኔታዎች ሁሉ ተስተካክለው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት ይዞታውን ለክለቡ አመራሮች እና ደጋፊዎች አስረክበዋል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የካቢኔ አባላትና የክፍለ ከተማው አመራሮች ተገኝተዋል። ክብርት ከንቲባዋም ክለቡ በውሳኔው መሠረት ከሰኞ ጀምሮ ይዞታውን ማስከበር እና ማጠር እንደሚችል ገልፀው የከተማ አስተዳደሩ ለከተማይቱ ህዝባዊ ክለቦች እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የልምምድና ሆስቴል ግንባታ ይዞታውን እንዲያገኝና እንዲያስከብር በተደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ፣ የከተማው የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን አቶ በላይ ደጀን፤ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ሮባ፤ የክፍለ ከተማው የሠላምና የፀጥታ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ደጀኔ ነጋሽ፤ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩን የካቢኔ አባላት፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮችና በዚህ ሂደት ጥረት ያደረጉትን ክለቡ አመስግኗል።
በተያያዘ መረጃ በቅርቡ ስራ የጀመረው ፈረሰኞቹ ስፖርት ባር አገልግሎቱ ላይ አዳዲስ ነገሮችን በመጨመር ስራውን አቀላጥፎ በመቀጠል ዛሬ ቅዳሜም በይፋ የሚመረቅ መሆኑን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
መረጃ
👇
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-