ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ጥሩ ጎል አስቆጥሪያለሁ ፣ ግን ደግሞ በቡድን ስራ ጥሩ ተጫወትን የመጣ ውጤት ነው ፣ አላህምዱሊላ” -ኦኪኪ ኦፊላፒ

የሲዳማ ቡናው ኢኪኪ አፎላቢ የሊጉን አራተኛ ጎል አስቆጥሯል።ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል ።

ጨዋታው እንዴት ነበር ?
ጥሩ ጨዋታ ነበር። ስለሁለም ነገር እግዚአብሔር ይመስገነው ጥሩ ነገር አሳክተናል። አላህምዱሊላ “
አራተኛውን ጎል እና የጨዋታ መክፈሻ ቢሆንም የጨዋታው አጨራረስ?
” ጥሩ ጎል አስቆጥሪያለሁ ፣ ግን ደግሞ በቡድን ስራ ጥሩ ተጫወትን የመጣ ውጤት ነው። በአጠቃላይ የቡድን ስራ በጥሩ አጨራረስ አጠናቀናል”
የረመዳን ፆም እየፃምክ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ከፃም ጋር መጫወት እንዴት ትገልፀዋለህ ?
” በርግጥ ከባድ ነው ፤ ግን ደግሞ እግዚአብሔር ይመስገነው። እየፆሙ መጫወት ተጨማሪ ሃይል ይሰጣል ። እግዚአብሔር ይመስገን”
ቀጣይ ጨዋታዎች በተመለከተ
” በቀጣይም ሶስቱንም ጨዋታዎች ማሸነፍ ነው የምንፈልገው። ከእግዚአብሔር ጋር ለማሸነፍ “