ዜናዎች

#ጌታነህ ከበደን ዳግም ወደ ብሔራዊ ለመመለስ የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል!

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል የነበረው ጌታነህ ከበደ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሚያሰለጥኑበት  ወራቶች ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ  ማግለሉን ተከትሎ በውቅቱ በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ነበር። 

በጊዜው ተጨዋቹ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር  በግልጽ  አለመግባባቶች  እንደነበሩ   ከተዘገበ በኃላ በመሃከላቸው  ሰላም መውረዱን አሰልጣኙ  በተለያዪ ጋዜጣዊ መግለጫዎች  ላይ  በመናገር   ነገር ግን  ጉዳዩ ከተከሰተ በኋላ  አሰልጣኝ ውበቱ ለጌታነህ ጥሪ  ሲያቀርቡ  ራሱን  ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን መገለፁን መዘገቡም ይታወሳል። 

  አሁን ላይ ደግሞ አዲስ የተመረጡት  የብሄራዊ ቡድኑ ጊዚያዊ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማሪያም እና ረዳታቸው ደግአረገ ይግዛው ጌታነህን ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ለመመለስ   ውይይት ማድረጋቸው  ስፖርት 52 ዘግቧል።
ጌታነህ አሁን ካለበት ወቅታዊ አቋምና በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ የነበረውን ሚና ከግምት በማስገባት ዛሬም ብሄራዊ ቡድኑን እንዲያገለግል አሰልጣኞቹ ፍላጎት ስለነበራቸው ስለሚመለስበት ሁኔታ ነበር በአካል ተወያይተዋል።

በአንፃሩ  ጌታነህ ወደ ቡድኑ ለመመለስ ዝግጁ አለመሆኑን መግለፁን ተከትሎ የአጥቂው መመለስ ሳይሳካ ስፖርት 52 ዘግቧል። ።