ዜናዎች

-ጉዳት ያስተናገደው ኤርትራዊው አሊ ሱሌይማን በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል!

አሊ ሱሌይማን
በኢትዮዽያ እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና የከፍተኛ የጎል አስቆጣሪነቱን በ4 ጎሎች የሚመራው ኤርትራዊው አሊ ሱሌይማን ዛሬ ቡድኑ ከዮጋንዳ ባደረገው የ5ኛ የደረጃ ጨዋታ  በ58 ኛው ደቂቃ ተጨዋቹ ጉዳት አስተናግዶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። የኤርትራ ከ 23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የፊት አጥቂ እና በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለመጫወት ከቀናት በፊት ለባሕር ዳር ከነማ የፈረመው ኤርትራዊው አሊ ሱሌይማን በአሁኑ ሰአት  ከጉዳቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
በሴካፋ የመክፈቻ ጨዋታ ባሳየው እንቅስቃሴ የበርካቶችን ተኩረት ወስዶ የነበረው እና በሴካፋ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ ለ ኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ሶስቱንም ጎሎችን በኢትዮዽያ ላይ አስቆጥሮ ሀትሪክ የሰራው አሊ ሱሌይማን ከዛሬው ጉዳት በኃላ አስፈላጊው የህክምና ተደርጎለት በመልካም ጤንነት የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል።
 በሴካፋ ውድድር በ6ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የኤርትራ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን  ሰሞኑን ወደ ሀገሩ የሚመለሱ ሲሆን ወጣቱ አጥቂ አሊ ሱሌይማን በቀጣይ ዓመት በቤትኪንግ ለአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ለመጫወት በጣና ሞገዶች ማሊያ የሚታይ ይሆናል።