ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ዲ.ኤስ.ቲቪ ቀጣይ ስርጭቱን የሚካሄድባት ድሬ ደርሷል!

የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ አዘጋጅ ከተማ ድሬዳዋ ዝግጅቷን የጨረሰች ይመስላል። ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግን  ጨዋታዎቹ በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፈው የሱፐር ስፖርት ተንቀሳቃሽ መኪናዎች ከባህርዳር ከተማ ወደ ድሬ  ገብተዋል።
 ተንቀሳቃሽ የቀጥታ ስርጭት ስቱዲዮ እና የካሜራ ባለሙያዎች ቡድን የመጀመሪያው ልዑካኑ ድሬዳዋ ገብቷል። የፊታችን እሑድ መጋቢት 27 ጀምሮ በድሬዳዋ የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ በቀጣይ ቀናት ቀሪ የዲ ኤስ ቲቪ  የልዑካን ቡድኑ ድሬዳዋ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለቡ መረጃ ክፍል መሠረት
የሱፐር ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ማስተላለፊያተንቀሳቃሽ መኪና ወደ ድሬዳዋ ሲገቡ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች በማጀብ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል ።
በተያያዘ ዜና የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ወደ ድሬዳዋ ሲደርሱ የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ሲሆን የተወሰኑ ክለቦቾም በድሬዳዋ ደርስወ ልምምድ እና ዝግጅታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።