ለ9 ሳምንታት በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ሲባል ተቋርጧል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ታህሳስ 16 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ በዲስፕሊን መመሪያው መሰረት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በ9ኛ ሳምንት የተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ሁሉም በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ 13 ግቦች በ12 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። በሳምንቱ 38 ተጫዋቾች/የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ የተገሰፁ ሲሆን 3 ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ ተወግደዋል።
በተጫዋቾች ቅጣት :
መሀመድ አብደልለጠፍ (ድሬደዋ ከተማ) ክለቡ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ፥ ዋኬኔ አዱኛ (አዲስ አበባ ከተማ) ክለቡ ከ ድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ኳስ በእጅን በመያዝ የግብ የማግባት አድል በማበላሸት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል
ግርማ ዲሳሳ (ባህርዳር ከተማ) ክለቡ ከ አዳማ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት እንዲከፍሉ ተወስኗል
ብሩክ በየነ(ሀዋሳ ከተማ) ክለቡ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ በ66ኛ ደቂቃ ላይ ግብ ካገባ በኋላ ደስታውን ሲገልፅ በውስጥ ልብስ ላይ ሃይማኖታዊ መልዕክት የሚያስተላልፍ ምስል በማሳየት ለፈፀመው ጥፋት ክለቡ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ብር 3000/ሶስት ሺህ / እንዲቀጣ ወስኗል።
በክለብ ደረጃ
ባህርዳር ከተማ ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ የክለቡ አራት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ እንዲሁም በተመሳሳይ ሃዋሳ ከተማ ክለቡ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ስድስት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት በከለብ ደረጃ 5000 /አምስት ሺ/ ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡
ሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ክለቡ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር በነበረው የ 9ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎችና የደጋፊ አስተባባሪዎች በጨዋታው መጠናቀቂያ ወቅትና ጨዋታቸው ካለቀ በኋላ ከፖሊስ ጋር ግጭት ስለመፍጠራቸውና ድንጋይ ስለመወርወራቸው ፣ የተለያዩ የስታዲየሙ ንብረቶች ላይ ጉዳት ስለማደረሳቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ። የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) ብር የ75 000 /ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ በሪፖርት ላይ የቀረቡትን የተነቃቀሉና የተሰበሩ ንብረቶችን እንዲያሰራ ወይም ባለንብረቱ አስልቶ በሚያቀርበው ዋጋ መሰረት ክፍያ እንዲፈፀም ወስኗል ።
@የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ