አትሌቲክስ ዜናዎች

#የ44ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዛሬ አሸኛኘት ተደረገለት!

በአውስትራሊያ – ባትረስ ከተማ እ.አ.አ ፌብሪዋሪ 18/2023 በሚካሄደው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ 14 ወንድና 14 ሴት አትሌቶች ከነተጠባባቂዎች በ40ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ተመልምለው ሆቴል ገብተው ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
አሸኛኘቱ ዛሬ በተከናወነ መርኃ ግብር በስዊስ ኢን ኔክሰስ ሆቴል በድምቀት ተካሂዷል።
አትሌቶች የኢትዮጵያ መታወቂያ የሆነውን ሰንደቅ አላማ በአደራ ተረክበዋል።