ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

👇
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ግንቦት 05 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 17 ጎሎች በ15 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 25 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።
በሳምንቱ በአምስት ተጫዋቾች ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል። አዲስ ግደይ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ መሳይ አገኘሁ(ባህርዳር ከተማ)፣ ብሩክ ማርቆስ(ሀዲያ ሆሳዕና) እና ዳዋ ሆጤሳ(ሀዲያ ሆሳዕና) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ፤ ናትናኤል ናሴሮ(ወላይታ ድቻ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።
በተጨማሪም ለወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና የቡድን መሪዎች የፕሪምየር ሊጉ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ በቀጣይ ቀናት ለማነጋገር ጥሪ አስተላልፏል።