ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

– የ2014 የውድድር ዓመቱን ባለሜዳዎቹ በድል ጀምረዋል! – ዳዊት የመጀመሪያው ቀይ ካርድ

የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 7 – ታህሳስ 15 ድረስ የመጀመሪያው ዙር ውድድር በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ ላይ የሚካሄድ ይሆናል።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ቀናት በሚካሄደው የ2014 ውድድር የመክፈቻ ጨዋታው በሜዳው ባለቤት አሸናፊነት ተጠናቋል።
በመጀመሪያውን ቀን የ2014 ቤትኪንግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ በ10 ቁጥሩ በመስፍን ታፈሰ ብቸኛ ጎል ጅማ አባ ጅፋርን 1 ለ 0 በማሸነፍ ዓመቱን በድል መጀመር ችሏል።
በጨዋታው ጅማሮ የተሻለ መንቀሳቀስ እና የጎል ሙከራ ያደረገው ሐዋሳ ከተማ በ15ኛው ደቂቃ የውድድር ዓመቱን ቀዳሚ ጎል አስቆጥሮ የመርሃግብሩ የመጀመሪያው ቀን በ3 ነጥብ ማጠናቀቅ ችሏል። ከመጀመሪያው አጋማሽ ብቸኛ ጎል በኃላ በሁለተኛው አጋማሽ በሁለቱም በኩል ብዙም የጎል ሙከራ ያልታየበት ጨዋታ ሆኖ ተጠናቋል። ከጨዋው መጠናቀቅ በፊት የጅማ አባጅፋሩ 10ቁጥር ዳዊት እስጢፋኖስ ኳስ ከጨዋታ ውጪ በኳስ አቀባይ ላይ የውሀ ፕላስቲክ ወርውሯል በሚል የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ቀይ ካርድ ሰለባ መሆን ችሏል-