የ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሊጠናቀቅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ቀርቶታል። የመጨረሻው ምዕራፍ በሀዋሳ ለመጀመር ሰአታት በቀረው የቤትኪንግ ውድድር ጋር በተያያዘ እንደተሰማው በዘንድሮው የ2013 በ6 ዘርፎች የኮከቦች ምርጫ በእግርኳስ መዘጋጀቱ ተሰምቷል። እንደሚታወሰው የዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከተለመደው የደርሶ መልስ አካሄድ በተለየ መልኩ ቡድኖች በተመረጡ በአምስቱ ከተሞች ጨዋታዎችን እንዲያደርጉ በተወሰነው መሠረት በአዲስ አበባ ስታዲየም ታኅሣሥ 3/2013 የተጀመረው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ነገ ሚያዚያ 28/2013 የመጨረሻው ምህራፍ በሐዋሳ ለማጠናቀቅ ይጀመራል።
ከአራት ወራት በፊት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተጀመረው ቤትኪንግ የ አዲስ አበባው የ6ቱ ሣምንታት ግጥሚያዎች 36 ጨዋታዎች ተደርገው 107 ግቦች ተቆጥረዋል። በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጎል ማስቆጠሩን የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በ22 ጎሎች ሲመራ የፋሲል ከተማው ሙጂብ ቃሲም በ19 ጎሎች ፣ ጌታነህ ከበደ በ 12 ጎሎች ይከተላሉ። የሊጉን የሻምፒዮናነት ፋሲል ከነማ በቀጣይ ጨዋታዎች ይፋ የሚያደርገው ይሆናል። በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በርካታ ወጣት እና ታዳጊ ተጨዋቾች በታዮበት ውድድር የኮከቦች ምርጫ መዘጋጀቱ ተሰምቷል።
በአገር ውስጥ በሬዲዮ የስፓርት ዘገባዎች ግንባር ቀደም የሆነው ስፓርት ዞን በስድስት ዘርፎች የ2013 የኮከብ ተጨዋቾች ፣ አሰልጣኞች፣ ጋዜጠኞች ጨምሮ ሌሎችም ያካተተ ምርጫ ለማካሄድ መታሰቡ ተሰምቷል። እንደ መረጃው ከሆነ የኮከቦቹን ምርጫ የስፓርት ቤተሰቡም የሚሳተፉበት እንደሚሆን ተነግሯል። ጉዳዩን በተመለከተ አዘጋጆቹ ስፓርት ዞኖች ተጨማሪ መረጃ በቅርቡ የሚያሳዎቁም ይሆናል።
Abubakar naser is outstanding player of this year and more opportunities has comes to him to play in high level of soccer league like eauropean so he has to deserve at least 4 trophies among 6 categories
mujib kassim is sepecial one
አቡኪ ነው ጎል ጨዋታ ተቃራኒ ቡድን በታክቲክ የሚያልፍ አመቻችቶ አቀባይ ለጎል የማይስገበገብ ከዳኞች ጋር ምርጥ ፀባይ እሺተኛ ብቻ ሁሉም ነገር የታደለ
Abuki magna adegna