ዜናዎች

የፌዴሬሽን ኃላፊዎች በእስራኤል :- ከትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች እና የመብት ተሟጋች ጋር ተገናኙ !

የሁለቱ አገራት የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች ስምምነቱን ሲያደርጉ

 

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ በፀሐፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንና  የፌዴሬሽኑ ባለሙያዎች የታከሉበት የልዑካን ቡድን በእስራኤል የተሳካ የወዳጅነት ግንኙነት ለማድረግ ባለፈው እሁድ ቴላቪቭ መድረሳቸው ይታወሳል።
በኢትዮጵያ እና በእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች መካከል ከረጅም ወራቶች በፊት በሀሣብ የነበረው ጅማሮ አሁን ተሳክቶ የወዳጅነት የእግርኳስ ጨዋታ እና በሁለቱ አገራት የትብብር ስምምነቶች የማጠንከር ስራ ለማስጀመር የሚረዱ ውይይቶች ተደርገዋል።
ሁለቱ አገራት ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ከ51 አመታት በኋላ ያደረጉት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች በድምር ውጤት 1 ለ 1 ተጠናቋል ።  ከዛሬው ጨዋታ በፊትም ሁለቱ ሀገራት ስምምነት አድርገዋል ፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን በኢትዮጵያ በኩል እንዲሁም የእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኦረን ሀሰን  የስምምነቱን መፈፀማቸው ታውቋል። የእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኦረን በስጦታ መልክ በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይም  ማልያም አበርክተዋል ።
ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ በእስራኤል የሚገኙ ትውለደ ኢትዮዽያውያን የእግርኳስ ባለሙያዎች እና አሁን ላይ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን በመገናኘት በይፋ ስኬታማ የሚባሉ ውይይቶች ታይተዋል ።በተለይም ከእስራኤል ትውለደ ኢትዮዽያውያን የእግርኳስ ባለሙያዎች ጋር የመጀመሪያ የተባለ ተሞክሮዎች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ትላንት ምሽትም መደረጉን ለጉዳዩ ቅርበት ካለው ማወቅ ችለናል።
ከቀናት በፊት በእስራኤል ሊግ የሚጫወተውን ትውለደ ኢትዮዽያዊ አጥቂ ስንታየሁ ስልልህን ያነጋገሩት የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ትላንት ምሽትም በተመሣሣይ በእስሪኤል እግር ኳስ ገና በወጣትነቱ እጅግ ተጠባቂ እና የብዙዎችን ትኩረት ጥሎ የነበረውን ታሪካዊ ትውለደ ኢትዮጵያዊ ተጨዋች ሂመያ ታጋ ጋር ተገናኝተው የተሳካ የተባለ ውይይት አድርገዋል።በአዲስ አበባ ተወልዶ ያደገውና አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገረው ሂመያ ታጋ ለእስራኤል ከ 17 እና ከ 21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫተ ቢሆንም ለዋናው ብሄራዊ ቡድን እጅጉን ተስፋ ተጥሎበት የነበረ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት የታሰበው ሳይሳካለት ቀርቷል።
በአሁኑ ሰአት ደግሞ በእስራኤል የታወቀ የሀበሾች የመብት ተሟጋች ሲሆን የኔታንያ ከተማ ምክር ቤት አባልም ነው። ታናሽ ወንድሙን ባለታወቀ ሁኔታ እሱ የታዳጊ ቡድን ተጨዋች በነበረ ሰአት በሞት ተለይቶት ፓሊስ ለቤተሰቡ ያረዳው።ተጨዋቹ በክለብ ለመጨረሻ ጊዜ እ.ኤ.አ በ 2017 ዓ.ም ለማካቢ ኔታንያ ተጫውቷል።
ይኸው ዝነኛ የቀድሞ ተጨዋች እና የአሁኑ የመብት ተሟጋች በትላንትናው ምሽት የኢትዮዽያ ልዑካን ባረፈበት ሆቴል ተገኝቶ የእራት ግብዣ እና በእስራኤል የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ በመወከል በቀጣይ በሁለቱም ሀገራት የወዳጅነት ግንኙነቶች እና አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ጅምሮችን በስፋት ተወያይተዋል።

ከምሽቱ የእራት ግብዣ በፊትም ታዋቂው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሂመያ ታጋ ለመጨረሻ ጊዜ የተጫወተበትን ክለቡን እና የከተማውን የማካቢ ኔታንያ ማሊያ እና ኳስ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ለአቶ ኢሳያስ ጅራ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር  በሆኑት አቶ ዓለሙ ረታ አማካኝነት በስጦታ አበርክቷዋል።