ዜናዎች

የፋሲሉ አማኑኤል በትላንቱ ግጭት ላልተወሰነ ጊዜ ከእግርኩዋስ እንደሚርቅ አሰልጣኙ ተናግረዋል!

ትላንት የ19ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ የኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ባደረጉት ጨዋታ የፋሲሉ ከነማው የአጥቂ መስመር ተጨዋች አማኑኤል ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ለህክምና ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።
የክለቡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስለ አማኑኤል ገብረሚካኤል የትላንት ምሽቱን ጉዳት አስመልክተው በማህበራዊ ገፃቸው ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል ።
” ጥቃቅን የሚመስሉ ጉዳቶች የጭካኔ ታክሎች ብዙዎችን ከህልማቸው አሰናክለዋል:: ለዚህ ከባድ ጥፋት ክእግዜር ቀጥሎ ተጨዋቾችን ህጉ ሊጠብቃቸው ይገባል::
አማኑኤል ገ/ሚካኤል በትላንቱ ግጭት ሁለት አጥንቱ ተሰብሮአል በዚህም ላልተወሰነ ጊዜ ከእግርኩዋስ መራቁ ግድ ሆኖአል::ተሽሎክ እንደምናይክ እምነቴ ነው ፈጣሪ ይማርክ”
የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውበቱ