አፍሪካ ዜናዎች

#የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከዋልያዎቹ ጋር በካይሮ የሚደርጉት ጨዋታ የክብር ጨዋታ ነው ሲሉ የግብፅ ሜዲያዎች እየዘገቡ ነው !

 

የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨምታውን ማለፉን ያረጋገጠውና ከኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በበርካታ ደጋፊዎቹ ፊት የሚግጠመው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ከዋልያዎቹ ጋር ነገ የሚያደረገው ጨዋታ በመጀመሪያው የማጣሪያው ጨዋታ ኢትዮጵያ ላይ ያጋጠመውን 2 ለ 0 ሽንፈት ለማካካስ የሚደረግ ታላቅ ጨዋታ እንደሆነ አል-መስሪ አል-ዩም የተባለ በድህረ ገፅ ዘግቧል።

የግብፅ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውን የምድቡ ቀዳሚ ሆኖ በ12 ነጥብ ማለፉን ቢያረጋግጥም የነገው ጨዋታበሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ዘንድ እየተጠበቀ እንዳለ እና ጨዋተው የክብር ጨዋታ እንደሚሆን ይኸው ድህረገፅ ዘግቧል።

በተጨማሪም ዘገባው እንደጠቀሰው በአፍሪካ ቻምፒዮና ማጣሪያ የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጉትን የነገ ጨዋታ የቀጥታ ሽፋን “BeIN Sports” ቻናል የሚተላለፍ መሆኑን ሲገለፅ ጨዋታው ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ 30,000 ተመልካች የመያዝ አቅም ባለው የአየር መከላከያ ስታዲየም ይካሄዳል ተብሏል።

ኢትዮ- ኪክ (ሊንኮቻችን)

#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን

tiktok.com/@ethiokick

#በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

#በኢንስታግራም ገጻችንን :-

https://www.instagram.com/ethio_ki

🔛ድረ ገጻችንን :-

Home page

One thought on “#የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከዋልያዎቹ ጋር በካይሮ የሚደርጉት ጨዋታ የክብር ጨዋታ ነው ሲሉ የግብፅ ሜዲያዎች እየዘገቡ ነው !

Comments are closed.