ዜናዎች

የግብፅ ሊግ ዛሬ ተጀምሯል- ሽመልስ በአዲሱ ክለቡ ነገ ጨዋታውን ያደርጋል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ሸመልስ በቀለ  የግብፅን ክለብ ኤል ጎውናን ከተቀላቀለ በኋላ ላለፉት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ለአዲሱ የውድድር ዓመቱ የዝግጅት እና የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። የአዲሱ የውድድር ዓመት የግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ መጀመሩን ተከትሎ ሶስት ጨዋታች ተደርገዋል። በመርሐ ግብሩም መሠረት የሽመልስ በቀለ ኤል ጎውናን ነገ ( ማክሰኞ )አመሻሽ ላይ በሜዳው ጨዋታውን ያደርጋል ።