አፍሪካ ዜናዎች

የጊኒ ቢሳው አሰልጣኝ ከኢትዮጵያ እና ከግብፅ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ማምሻውን ተጫዋች ከስፔን ጨምረዋል!

 

ኢትዮጵያን በሜዳዋ የምታስተናግደው ጊኒ ቢሳው ከኢትዮጵያ እና ከግብፅ ጋር ለምታደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ቦአ ሞርቴ በብሔራዊ ቡድን ላይ ማምሻውን ለውጦችን አድርጓል።

ለብሔራዊ ቡድኑ ዝርዝር ላይ የነበሩት ማውሮ ቴይሼራ እና ጃርዴል በጉዳት ምክንያት : ካርሎስ ማኔ እና ዳልሲዮ በግል ምክንያቶች ተሰናብተዋል።

አሰልጣኝ ሉዊስ ሞርቴ በወጡት ተጫዋቾች ምትክ በስፔን La Liga 2, የሚጫወተው የ20 ዓመቱን ታዳጊ የፊት መስመር ተጨዋች ማርሲያኖ ቻሚ እና በአገር ውስጥ ሻምፒዮና ላይ የሚጫወቱትን ሁለት ተጫዋቾችን ሴኔ ካማራ እና ባካሪን አጥቂ ጠርተዋል።

አሰልጣኙ ማምሻውን ይፋ ያደረጉት የጨዋቾች ዝርዝር ምስሉ ላይ ይመልከቱ