ዜናዎች

የድሬዳዋ ከተማ ለቤትኪንግ እንግዶች እና አስተዋጽኦ ላደረጉ ልዩ ስጦታና የምስጋና ሰርተፍኬት አበረከተች !

በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አራት ጨዋታዎች ብቻ ይቀሩታል። አራተኛው ዙር ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ያስተናገደችው ድሬዳዋ ከተማ አስተዋጽኦ ላደረጉ የእውቅና ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ውድድሩ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ የሚዲያ ባለሞያዎች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት የምስጋናና የእውቅ ፕሮግራም በአስተዳደሩ በኩል ዛሬ ተደርጉል፡፡
የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ በዲኤስ-ቲቪ አማካኝነት ስርጭቱን መተላለፉ ከጀመረ በኋላ በርካታ የእግር ኳስ ተመልካቾች ጨዋታዎችን መመልከት  መቻላቸወ በዚህም ውድድሩን በምሽትም በማካሄድ በኢትዮጲያ እግር ኳስ ሌላ ታሪክ ማስመዝገብ መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር ገልፀዋል ፡፡
ከስፖርታዊ ውድድሮችና ውጤቶች ባሻገር እግር ኳሱን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን በማሻሻል የሀገር ልማት ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ ለወጣቶችም የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ሰፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ በተዘጋጀው የምስጋና የእውቅና ስነ ስርዓት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ለውድድሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ የፀጥታ አካላት ፣ ጋዜጤኞችና ፣ ለዲኤስቲቪ አባላት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ሼር ካንፖኒ ከእለቱ የክብር እንግዶች ልዮ ስጦታና የምስጋና ሰርተፍኬት መበርከቱን  የስፖርት ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል ።