
በደርቢ ጨዋታ ጎል በማስቆጠሩ የተሰማው ስሜት ?
” ስሜቱ በጣም ደስ የሚል ነው። በእኔ ጎል ማሸነፋችን ደግሞ በጣም ደስ ብሎኛል ። በጣም ደስ የሚለው ደግሞ ደርቢ ላይ ስታስቆጥር ነውና የተለየ ስሜት ነው የፈጠረብኝ።
ከጨዋታው በፊት በስፑር ስፖርት በሙሉ ልብ እናሸንፋለን ብለህ ነበር : የተለየ የ9 ቀናት ዝግጅቱ ነው ለዚህ ውጤት ምክንያት ?
” አዎ …ከጨዋታው በፊት ባደረኩት ቃለ ምልልስ እንደምናሸንፍ እርግጠኛም ሆኜ ነበር። አንደኛው ዙር ላይ ያጣነውን ውጤት ለደጋፊያችን ለመካስ በሙሉ ስሜት ነበር የተነሳሳነው እና የገባነው ። ከቆየነውም የልምምድ ሁኔታ አንፃር እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ነበርንና ያ ደግሞ ያስታውቅ ነበር የቡድኑ መንፈስም እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ነበርኩ ለዛም ነው ከጨዋታው በፊት የተናገርኩት።
ለደጋፊዎች የሚያስተላልፈው መልዕክት ?
“የደርቢ ጨዋታው ከአዲስ አበባ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተካሄደው። ለደጋፊዎቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት የምፈልገው ። በቦታው ባይገኙም በቀጥታ እንደሚከታተሉ እናውቃለን በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።
ያስቆጠርካት ጎል ለማን ትሁን ?
” ለእናቴ እና ለምወዳት ጓደኛዬ እንዲሁም ለደጋፊዎቻችን ይካፈሉት አንድም ብትሆን ትበቃለች … ( በፈገግታ)….
