በሞሮኮ አስተናጋጅነት በ2024 ለሚካሄደው የአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ ለመግባት ሉሲዎቹ የመጀመርያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ነገ ከቡሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በ9:00 ሰዓት ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የነገን ጨዋታ እና የቡድኑን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች
– የቡድኑ ዝግጅት በተመለከተ
“የ2024 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ከጀመርን ወደ 15 ቀናት ያክል ሆኖናል። በዚህ ጊዜ ልጆቹን ይዘን ዝግጅት ለማድረግ ሞክረናል ፣ ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች በተለይ የሜዳ ችግሮች ፣ የክረምቱ ወቅት መሆን በተሸላ የአየር ሁኔታ ለመስራት ተቸግረን ነበር።
በነበረን 12 ቀናት የወጣቶች አካዳሚ የሁልጊዜ ተባባሪያችን ባላቸው አቅም ሜዳውን ፈቅደውልን ነበረ ፣ ሆኖም ሜዳውን የራሳቸውን ተጨዋቾች ስካውት የሚያደርጉበት ስለነበረ እዛ ሜዳ ላይ ለአራት ቀናት መስራት አልቻልንም። አበበ ቢቂላ ሜዳም ላይ የሲቲ ካፕ እና አንዳንድ ውድድሮች ሜዳው በመያዙ ምክንያት ነበር።
“ይህንን ምክንያት ስናገር አንዳንድ ነገሮች አልሰራንም የሚለውን ሰበብ ለማቅረብ አይደለም።ቡድኑ ሁለት ዓይነት ቡድን ነው. 1ኛው ተዘጋጅቶ የመጣ ቡድን አለ። የተወሰኑ ተጨዋቾች ውድድሮች ላይ የነበሩ ፣ ሌላው ደግሞ ከዕረፍት ላይ የመጡ ተጨዋቾች ነበሩ። ስለዚህ ሁለቱንም የማቀናጀት ችግሮች ነበሩ ። ያው ሴቶች እንደመሆናቸው መጠን የተወሰነ ጊዜ ሲያርፉ የራሱ የሆነ ተፅኖ ይኖረዋል። እሱ እሱ ተደምሮ ስምንት ውድድር ላይ ከነበሩ ልጆች በአጠቃላይ ከ26 ከተጠሩት ጋር ለማቻቻል ጥረት አድርገናል።
– የአፍሪካ ዋንጫ ያማከለ ዝግጅት ስለማድረግ
“ከጨዋታ ርቀው ለመጡ ተጫዋቾች ብዙ ቀን ነው ። ግን ምንድን ነው በተቀመጠው ሳይንስ መሰረት በዚህ ቀን ውስጥ እንዴት ቡድን ሠርቶ ለጨዋታ ማቅረብ እንደሚቻል ስለማውቅ ። በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የሜዳ ችግሮች እና ከጨዋታ ርቀው የመጡ ተጫዋቾችን ይዘን ነበር ዝግጅት ያደረግነው ። የተሟላ ዝግጅት አድርገሃል ወይ ለሚለው ምላሼ አላደረኩም ነው”
– የሜዳ ችግሮች ስለምቅረፍ የተደረጉ ጥረቶች ነበሩ ወይ?
“በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የተሟላ ዝግጅት አላደግንም ምክንያቱ ደግሞ የሜዳ ችግር የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሲቲካፕ እየተካሄደበት ሲሆን አሁን እየሰራንበት ያለው የወጣቶች አካዳሚም በሚገባ መዘጋጀት አልቻልንም ። የሜዳ ችግሮችን ለመፍታት ተቋሙ በደብዳቤ ጭምር ይሄዳል ። ነገር ግን ተቋሙ ሳይሆን እዛ ጋር ያሉት የሜዳው ኃላፊዎች ከእኛ ቀድመው ሜዳው ላይ ፕላን እንደተያዘ ነው ያሳወቁን ። ያንን ፕላን ደግሞ እኛ ማስቀየር አንችልም። ተቋሙ ደግሞ ፕላኑን ማስቀየር ባለበት ፣ውድድር ስነስርዓት መሠረት ነው ስለዚህም የአበበ ቢቂላ ሜዳው በዛ መልኩ የራሱ የሆነ ፕላን ስለተያዘ ነው።
-የአፍሪካ ዋንጫ የመግባት ፕላናችሁ
“ቅድም እንዳልኩት ቡድኑን በ10 ቀናት አዘጋጅቼ የአፍሪካ ዋንጫ ለመግባት ከባድ ቢሆንም ሃሳባችን ባሉን ጊዚያት ፣ባሉን ቀጣይ ጨዋታዎች ተጠቅመን የአፍሪካ ዋንጫ መግባት ነው ፍላጎታችን ። በአብዛኛው ትኩረት አድርገን እየሰራን ያለነው የአፍሪካ ዋንጫውን ለማለፍ ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ከተገባ በጣም ቆይቷል። ስለዚህ የዚህኛው ትውልድ ዋነኛ ዓላማው የአፍሪካ ዋንጫ መግባት ነው። በዚህ አጋጣሚ በጣም ደስተኛ ነኝ ። ተጨዋቾቼንም ፣በዚህ አጋጣሚ ማመስገን እፈልጋለሁ። ውጤታማ ይሆናሉ ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።
የሜዳ አድቫንቴጅ በተመለከተ
” የሜዳ አድቬንቴጅ በዘመናዊ እግርኳስ የሜዳ ላይ ጨዋታን አሸንፎ ውጤት አመጣለው ማለት ከባድ ነው። ኳሷም፣ ጎሉም ሜዳውም ለሁለታችንም እኩል ነው። እናም ሰርተን ማሸነፍ ስንችል ብቻ እንጂ ሜዳው የእኛ ስለሆነ እናሸንፋለን ማለት አይደለም።”
የውል ዘመኑ ስመጠናቀቁ
” የውል ዘመኔን በተመለከተ ቀጣይ የምሰራቸው ፕላኖች አሉ። እሱን ለሚመለከታቸው አካላት present አድርጌ የሁለት ዓመት የውል እ ከዚህ ቀደም ከሰራሁት ስራ ጋር ዕውቅና በመስጠት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ተስማማምቼ ወጥቻለው። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ሁሉም ነገር መፍትሄ ያገኛል። በዚህ አጋጣሚ ያቀረብኩት ዓሳብ recognitions ለሰጡኝ የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ምስጋና አቀርባለሁ ” በማለት በመግለጫው ላይ ተናግራል