ዜናዎች

” የዘንድሮውን ቤትኪንግ ፋሲል ከነማ ይበላዋል የሚል ግምት አለኝ ” -አሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን

የአሰልጣኝ ፍስሀ  ጥዑመልሳን   ከድሬደዋ ከተማ መሠናበት  በኃላ  በጤንነታቸው ላይ ትንሽ ችግር ገጥሟቸዋል ነበር። በአሁኑ ሰአት በምን ሁኔታ ይገኛሉ የሚለውን  እና  የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን ማን ያሸንፋል በሚለው ዙረያ  ከእአሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን ከኢትዮ ኪክ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ኢትዮኪክ :- አሰልጣኝ ፍሰሃ  በአሁኑ ሰአት በምን ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው ? አዲስ ቡድን ይዘሃል ?
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- አይ ..ጅማ ላይ ሳሰለጥን ትንሽ ወገቤን አያመመኝ ማደንዘዣ መርፌ እየተወጋው ነበር የማሰራው። እዘህ ስመጣ ኩላሊት ነው ብለውይኝ ትንሽም ቆስሎ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ተከልክዬ እረፍት ላይ ነኝ። እና አሁን እየተሻለኝም ነው።
ኢትዮኪክ :- በዚህ አጋጣሚ ዕረፍት ላይ መሆንም ጥሩ ነው ማለት ነው ?
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- አዎ ባጋጣሚ ይህ ዕረፍት ባይመጣ ኖሮ ለስራው ስለምጓጓ ማደንዣ እየወሰድኩኝ እቀጥል ነበር። ሌላው ደግሞ ኩላሊት መሆኑንም አላውቀውም ነበር። በኃላ ዶክተሩ ከህይወትህ ይበልጣል እንዴ ቆስሏል ብሎ ነገረኝ። እውነትም ማደንዣውን ሳቆም መንቀሳቀሰም አቅቶኝ ነበር። አዲስ አበባ ሄጄ ተመርምሬ ነው እግዚአብሔር ይመስገነው ያወቁት።ኮብል ስቶን ላይ ስራመድ ያመኝ ነበረ።ግን አሁን ደህና ነኝ።
ኢትዮኪክ :- የቤትኪንግ ውድድር ድሬ ላይ ተጀምሯል ፤ በዚህ ላይ ምን የምትለኝ ነገር ይኖራል ?
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- ድሬ ላይ ያየሁት ነገር ህዞቡ በደማቅ አቀባበል በማድግ ነበር የተቀበለው።ሌላው ከሌላው ለየት ያለ ነገር ያየሁት አብዛኞቹ ክለቦች የዚህ አገር ሰው የሆነ የራሳቸው ደጋፊ አላቸው። በተለይም ቡና በከፍተኛ ሁኔታ ደጋፊዎች አሉት። እንዲሁም ፋሲል ፣ ጊዮርጊስ ብዙ ደጋፊዎች አሏቸው። ሌላው ድር እኛ ስንጫወት ነበር በመብራት ጨዋታ የማውቀው በስንት አመቱ አሁን ድሬ ላይ ይታያል። አሁን የሙቀት ጊዜ ነው ድሬደዋ ከፍተኛ ሙቀት አለ ። ስለዚህ አንደኛው ጨዋታ 10:00 ሰአት ሌላው ጨዋታ 1 :00 መሆኑ ጥሩ ነው። ትላንት የቡናንም የጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታዎች አይቻለው ። ስለዚህ ይህ መልካም ነገር ነው። በቀጥታም ጨዋታው ከዛሬ ጀምር ይተላለፋል።
ኢትዮኪክ :- የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን ማን ያሸንፋል ብለህ ትገምታለህ ?
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- ዋንጫው እኮ ትላንት የጊዮርጊስ እና የቡና ነጥብ መጣል ግምቱኔ ወደ ዘጠና በመቶው ወደ ፋሲል አድርሶታል። የዛሬውን ጨዋታ ደግም ድቻን ካሸነፈ ልዪነቱ እየሰፋ ይሄዳል። ስለዚህ በዚህ በሚፈጠረው ልዮነት ላይ ለመድረስ ይከብዳል። እያንዳንዱ ጨዋታ ጠንካራ ነው። እያንዳንዱን ጨዋታ ክለቦች በጥንቃቄ ነው የሚጫወቱት። ምክንያቱም ከላይ ያሉት ዋንጫ ይፈልጋሉ ፤ ከስር ያሉት ላለመውረድ። ይህንን በትላንቱ ጨዋታ አይተናል። ቡናም ባለቀ ሰዓት ነው የገባበት። የመጀመሪያው ጨዋታም በጣሜ በጥንቃቄ ባዶ ለባዶ ያለቀው ። ስለዚህ ሌላውም የሚቀጥለው በዚሁ መሰሠት ስለሆነ ከዚህ በኃላ ነጥብ በተጣለ ቁጥር ከባድ ነው።ስለዚህ የዘንድሮውን ቤትኪንግ ፋሲል ይበላዋል የሚል ግምት አለኝ።
ኢትዮኪክ:- የድሬደዋ ከተማ ቡድንስ በዘንድሮ ሊግ የመቆየቱን ነገር እንዴት ታየዋለህ ?
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- በሊጉ ይቆያል ብዬ እገምታለሁ። ምክንያቱም እኔም በነበርኩ ጊዜ የነበሩ ጥቃቅን ችግሮች ነበሩ። እንዲሁም የተጨዋቾች ጉዳት ነበሩ። ዛሬ በፌስቡክ እንዳየሁት በረከት ይገባል ። ይሄ ለኛ አንዱ ጥንካሬ ነው። ያሰጋዋል ብዬ አላሳብም። በሜዳችን መጫወታችን አድቫንቴጅ ነው ደጋፊ ባይኖርም። ስለዚህ ቡድናችን አያሳስውም እላለሁ።
ኢትዮኪክ :- የኮቪድ መጨመር ጋር ውሳኔዎች እየተላፉ ነው
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- አሁን ካለው የኮቪድ አሳሳቢነት ሰው መከልከሉ ትክክል ነው እላለሁ። በስታዲየሙ ውስጥ የተፈቀደላቸው 10 ደጋፊዎች ሲጨፍሩ ተጣብቀው ነው። ከዛ አንፃር ውሳኔውን ትክክል ነው እላለሁ። እግር ኳስ ስሜት ስለሆነ የሚደረገው አይታወቅም እና ለጥንቃቄ ሲባል ልከ ነው።
ኢትዮኪክ :- በዚህ አጋጣሚ ጤንነትህ ተመልሶ ወደስራ እንድትመለስ ፈጣሪ ይርዳህ እንላለን አመሠግናለሁ።
አሰልጣኝ ፍሰሃ:- አሜን እኔም አመሠግናለሁ።

One thought on “” የዘንድሮውን ቤትኪንግ ፋሲል ከነማ ይበላዋል የሚል ግምት አለኝ ” -አሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን

Comments are closed.