አፍሪካ ዜናዎች

#የዓለማችን 4ኛው ውድ ዋንጫ የአፍሪካ ዋንጫ ድዋላ ደርሷል !

በካሜሩን አዘጋጅነት በፈረንጆቹ ከJanuary 9 ተጀምሮ February 6 የሚጠናቀቀው የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር 10 ቀናት ቀርተዋል።

አዘጋጇ ሀገር ካሜሩንም ውድድሩን ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ ለማካሄድ እንግዷቿን መቀበልም የጀመረች ሲሆን በካሜሩን የተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች በዓለማችን አምስተኛ ውዱ የሆነው የአፍሪካ ዋንጫም ለህዝብ በክፍት መኪና ለእይታ አየቀረበ ሲሆን አሁን ላይ ዋንጫው ከሊምቤ ወደ ሁለተኛ ዋና ከተማ ዱዋላ የደረሰ ሲሆን ቀጥሎ የመክፈቻ ስነስርዓት የሚካሄድበት ያዎንዴ ከተማ የሚያደርግ ይሆናል ።

 

በነገራችን ላይ የአፍሪካ ዋንጫ ዋጋውን ያውቁ ኖሯል ?

ምናልባት በብዙዎች ዘንድ የውድድደሩ አሸናፊ ሀገር የሽልማት ገንዘብ (4.5 ሚሊዮን ዶላር) እንደሆነ ይታወቅ ይሆናል ነገር ግን የዋንጫውን ዋጋ ላይታወቅ ይችል ይሆናል።

እንደ ዌ ስፖርት ዘገባ ከሆነ የአፍሪካ ዋንጫ በአለም እግር ኳስ አራተኛው ውድ ዋንጫ ነው ይለናል። የዋንጫው ዋጋውም 150,000 ዶላር ነው።

በዓለም ላይ ካሉት አምስት ውድ የእግር ኳስ ዋንጫዎች ከዚህ በታች የተቀመጡ ሲሆን አሁን በካሜሩን አሸናፊውን የሚጠብቀው የአፍሪካ ዋንጫ በዓለም ውድ ዋንጫዎች አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

የዓለማችን ውድ ዋንጫዎች
👇

-በቀዳሚነት የዓለም ዋንጫ – 20,000,000 ዶላር

-2ኛ የኤፍኤ ዋንጫ – 1,180,000 ዶላር

– 3ኛ የባሎንዶር ዋንጫ – 600,000 ዶላር

-4ኛ የአፍሪካ ዋንጫ – 150,000 ዶላር

– 5ኛ የሴሪ ኤ ዋንጫ – 66,000 ዶላር

#የይህን የዓለማችን አራተኛ ውድ የአፍሪካ ዋንጫ ማን ያሸንፍ ይሆን ?