ዜናዎች

የውልቂጤ ከነማ አውቶብስ ድሬ ላይ ለእስር ተዳርጓል!

በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው  የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር  ከአራት  ተስተካካይ ጨዋታዎች በኋላ በቻን ውድድር ሊጉ ለጥቂት ሳምንታት ተቋርጦ  ወደ አዳማ ከተማ የሚዞር ይሆናል።
እናም ቡድኖች በድሬ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው በመውጣት ላይ ቢሆኑም  የወልቂጤ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ግን ለሊጉ ውድድር ድሬዳዋ በቆየበት ወቅት በካራ ማራ ሆቴል ያረፈበትን መክፈል ባለመቻሉ አውቶቡሱ ለእስር መዳረጉ ተሰምቷል።

ላለፉት አራት ወራት የተጨዋቾች ደሞዝ ካለመክፈል ጋር ክለቡ ስሙ መነሳቱ ሲሰማ አሁን ደግሞ  የሆቴል ቆይታ ጋር በተያያዘ የስፖርት ቡድን መጓጓዣ እንደዋስ ለእስር ተዳርገዋል።

አውቶቡሷ ከዚህ ቀደም በሃዋሣ፣ባህርዳር እና አዲስ አበባ ለእስር ተደርጎ እንደነበር መረጃው ያመለክታል።

@habtamu abera
መረጃ
በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

በኢንስታግራም ገጻችንን  :-
https://www.instagram.com/ethio_kick

🔛ድረ ገጻችንን  :-

Home page