አፍሪካ ዜናዎች

የዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ሱዳንን 3-2 አሸንፏል! – ቀጣይ ተጋጣሚያቸው የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ካሜሩን ገብቷል

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ይረዳውዘንድ የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር አድርጎ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሁለት ጎሎችን ሽመልስ በቀለ አንድ ጎል በአጠቃላይ 3 ለ2 አሸንፏል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶቻቸው በዛሬው ጨዋታ የቡድናቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም የቡድኑን ቀጣይ መሻሻል ያለበትን በተወሰነ መልኩ ያዪበት አጋጣሚ ነው ተብሎ ይገመታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ከዙምባቡዌ ጋር ያደረጋል። የዙምባቡዌ ብሔራዊ ቡድንም በአፍሪካ ዋንጫ እና በቅድመ ዝግጅት እንዲሁም ለወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ካሜሩን ገብቷል።