ዜናዎች

#የዋልያዎቹ ቀጣይ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ !

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ በጊዜያዊነት እንዲመሩ የኢ/እ/ፌ ቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና እና ረዳት አሰልጣኝነት መሾሙ የሚታወስ ሲሆን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ይፋ እንደሚያደርግ ባሳወቀው መሠረት በቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት እየሰሩ የሚገኙትን እና ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድኑ ልምድ ያላቸውን አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝን ሾሟል።